Adiam berhane
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Adiam berhane, Health/Beauty, Addis Zemen.
ይህንን ያውቃሉ።
03/07/2023
ይነበብ
❇️ የጀርባ ህመምን በቀላሉ ለማከም ❇️
******************************
አብዛኛውን ጊዜ በእድሜ፣ በአደጋ እንዲሁም ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የጀርባ ህመም ሊከሰት ይችላል።
የጀርባ ህመምን በህክምና አሊያም በቀላሉ በቤታችን ውስጥ ማከም የምንችል ሲሆን፤ እኛም ዛሬ የጀርባ ህመምን በቀላሉ በቤታችን ለማከም የሚረዱን የተለያዩ ዘዴዎችን እንጠቁማችሁ።
1️⃣ ጀርባችንን ከቅዝቃዜ መጠበቅ
ለረጅም ጊዜ ሲያስቸግረን የቆየ የጀርባ ህመም ካለብን ሁሌም ጀርባችንን ብርድ እንዳይመታን ተጠንቅቀን ሙቀቱን መጠበቅ አለብን።
ለዚህም ይረዳ ዘንድ አዘውትረን ትኩስ የሆኑ ምግቦችን ብቻ እንድንመገብ ይመከራል።
2️⃣ ነጭ ሽንኩርት መመገብ
በየዕለቱ ምግባችን ውስጥ ነጭ ሽንኩርት እንዲገባ አድርግን መጠቀም፤ ለጀርባ ህመም ፍቱን መሆኑን የጤና ባለሙዎች ይመክራሉ።
3️⃣ በሶብላ ለጀርባ ህመም ፍቱን መሆኑም ተነግሯል
በሶብላውን በውሃ ውስጥ በመጨመር በደንብ እንዲፈላ ካደረግን በኋላ ለብ እንዲል አድርግን ጨው በመጨመር መጠጣት ጀርባ ህመምን ለማከም ይረዳል ተብሏል።
4️⃣ በባህር ዛፍ እና በሰናፍጭ ዘይት መታሸት
በባህር ዛፍ እና በሰናፍጭ ዘይት ጀርባን መታሸትም የጀርባ ህመምን ለማከም ይረዳል።
5️⃣ ጀርባችንን መታሸት
ማንኛውንም አይነት መታሻ በመጠቀም ጀርባን መታሸትም ህመሙን ለማስታገስ እንደሚረዳ ተጠቅሷል።
6️⃣ ቦንድድ ወይም ጠበቅ ያሉ ፍራሾችን መጠቀም
ቦንድድ ወይም ጠበቅ ያሉ ፍራሾች ላይ መተኛት የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖረን በማድረግ የጅርባ ህመምን ይቀንሳል።
7️⃣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግም ሌላኛው የጀርባ ህመምን ለማከም ወይም ለመቀነስ የሚረዳን መንገድ ነው።
መልካም ጤንነት!!
ወቅታዊ እና የተሟሉ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት፤ይከታተሉ:-
ሊይታይ የሚገባ
Category
Website
Address
Addis Zemen
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Adiam berhane posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.