Tena Holistic
Chronic disease starts at the cellular level. The root cause is metabolic, and so is the solution. Reclaim your health! 09-82-22-4444
High-carb diets and sedentary lifestyles drive metabolic syndrome (insulin resistance, hypertension, diabetes, obesity).
ምን እንብላ ???
የጤና ወታደሮች ቻሌንጅ
ካለዘይት ምግብን መስራት!
ፆም ለመንፈሳዊም ለስጋዊም 👌
07/08/2026
የትናንት ምሳዬ (ከዉስጥ ቅልቅል የተቀቀሉ አትክልቶች አሉ)::
ለጤናችን በጣም አሳሳቢ ነዉ!!
05/08/2026
«ሱፐርፉድ» (Superfood) የሚባሉት ምግቦች ለጤናችን ተአምር ይሰራሉ ወይስ የገበያ ማስታወቂያ ማጋነን ናቸው? 🤔🍎
ብዙዎቻችን «ሱፐርፉድ» ተብለው የሚሸጡ ውድ የውጭ አገር ምግቦች (እንደ ስፕስፒሩሊና (Spirulina)፣ ቺያ ሲድ) ለጤናችን የግድ አስፈላጊ ናቸው ብለን እናስባለን። ነገር ግን እውነታው ከዚህ በተለየ መንገድ ነው፡
✅ አንድ ታምር የስሚሰራ መለኮታዊ ምግብ የለም፤ የተለያዩ ምግቦች ጥርቅም፣ መፈራረቅ እና መመጣጠን ግን በጊዜ ሂደት እንደ ልማድ ስንመገባቸው ለጤናችን ተዓምር ይሰራሉ።
✅ ዋናው ሚስጥር ብዝሃነት ነው፡ ጤናማ አመጋገብ የሚመጣው ከአንድ ነጠላ «ተዓምረኛ» ምግብ ሳይሆን፣ ከተለያዩ የቀለም ዓይነቶች፣ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች፣ ሙሉ እህሎች እና ጤናማ ቅባቶች ውህደት ነው።
✅ ተራ ምግቦች ከውድ ምግቦች እኩል ናቸው፡ እንደ ቺያ ሲድ ወይም ስፒሪሉና ያሉትን ውድ ምርቶች መግዛት ሳያስፈልግ፣ በአካባቢያችን በቀላሉ የምናገኛቸው እንደ የተፈጨ የተልባ ዘር (Flaxseeds)፣ ስፒናች፡ ጎመን እና ብሮኮሊተመሳሳይ አልያም የተሻለ ጥቅም ይሰጣሉ።
✅ ተጨማሪ ምግቦች ተጨማሪ (supplements) ናቸው፡ እንደ ስፒሩሊና ወይም ማቻ ያሉትን መጨመር ደስ የሚልዎት ከሆነ ይቀጥሉበት፤ ነገር ግን እነሱ መሠረታዊ የምግብ መሠረት ሳይሆኑ እንደ ማጠናከሪያዎች ብቻ መታየት አለባቸው።
ውድ የውጭ አገር ዱቄቶችን በመፈለግ ከምንባክን፣ የዕለት ተዕለት ምግቦቻችንን በጥራት እና በብዝሃነት ማዘጋጀት ለጤናችን ይበልጥ ጠቃሚ ነው።
ጤና ይስጥልን!
Dr Markos
04/08/2026
ጤና ይስጥልኝ!
💡 "ካሎሪ ቀንሼ እያለ ክብደቴ ለምን አልቀነስ አለ?" (ከstatic Calorie Deficit or CICO ወደ Dynamic የNIH Neuro-endiocrine ሞዴል)
ብዙዎቻችን «በቀን 500 ካሎሪ ብቀንስ በሳምንት ግማሽ ኪሎ፣ በዓመት 24 ኪሎ እቀንሳለሁ» የሚለውን የቆየ የቀመር ህግ እንሰማለን። ነገር ግን በተግባር ሲሞከር የተወሰነ ቀንሰን ክብደታችን በአንድ ቦታ ይቆማል (Plateau)! ለምን ይመስላችኋል?
ምክንያቱም የሰውነታችን ሜታቦሊዝም እንደ ሂሳብ ማሰቢያ (Calculator) ቀጥተኛና ቋሚ ስላልሆነ ነው!
በአዲሱ የNIH (የአሜሪካ ብሔራዊ የጤና ተቋም) ምርምር መሠረት፡
1️⃣ ሰውነታችን ይቀየራል፡ ክብደት በሚቀንስበት ጊዜ ሰውነታችን የካሎሪ ማቃጠል አቅሙን በራሱ ይቀንሳል (Adaptive Thermogenesis)።
2️⃣ የካርቦሃይድሬት እና ኢንሱሊን ተፅዕኖ፡ ካርቦሃይድሬት የበዛበት ምግብ ስንመገብ ኢንሱሊን ይጨምራል፤ ይህ ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ ያለው ስብ እንዳይቃጠል የሆርሞን "ቁልፍ" ይዘጋበታል።
3️⃣ የርሀብ ሆርሞኖች ይነሳሉ፡ ሌፕቲን (Satiety Hormone) ሲቀንስና ግሬሊን (Hunger Hormone) ሲጨምር አእምሮአችን የረሃብ አደጋ እንደተደቀነበት በማሰብ ምግብ እንድንፈልግ ይገፋፋናል።
በአጭሩ፡ ክብደት መቀነስ ቀጥተኛ መስመር ሳይሆን የሆርሞኖች እና የሰውነታችን የተፈጥሮ መከላከያ ስርዓት ውጊያ ነው!
ይህንን ሳይንሳዊ እውነታ፣ የካሎሪ እና የሆርሞኖችን ሚስጥር እንዲሁም ለምን አትሌቶች እና ተራ ሰው የተለየ ውጤት እንደሚያዩ በጥልቀት የተተነተነበትን ሙሉ ሰነድ (Document) ማንበብ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያገኙታል👇
(በአማርኛ ከፈለጉ comment ላይ "Amharic" ብላችሁ ጠይቁኝ።)
🔗 ሙሉ ሰነዱን ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡ ወይም copy አርገው ብራውዘር ላይ paste ያርጉት፡ 👇
https://drive.google.com/file/d/1uLp-NBvxkakWlmyynUw_w1QXekO46eZb/view?usp=sharing
#ጤና #ክብደትመቀነስ #ሜታቦሊዝም #የጤናመረጃ
By Dr Markos
04/08/2026
📌 ክኖር (Knorr) እና መሰል የምግብ ማጣፈጫዎች ለጤናችን ምን ያህል ደህና ናቸው?** 🍲✨
(***🚨 ማስታወሻ፡ ክኖሮች፡ ይህ መረጃ open source ነው። በተደጋጋሚ ከተከታዮች ስጠየቅ ስለነበር open source info share እያደረኩ ነው።***)
በየዕለቱ በምግብ ዝግጅታችን ወቅት ጣዕም ለመጨመር በስፋት ከምንጠቀምባቸው ነገሮች አንዱ "የክኖር ኩብ (Bouillon Cube)" ነው። ነገር ግን በየቀኑ አብዝቶ መጠቀም ከጤና አኳያ ምን ጉዳቶች አሉት?
እነሆ ልናውቃቸው የሚገቡ 3 ዋና ዋና ነጥቦች:
1️⃣ ከፍተኛ የጨው (Sodium) መጠን፡
በነዚህ ማጣፈጫዎች ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ጨው ይገኛል። አብዝቶ መጠቀም ደግሞ ለደም ግፊት መጨመር፣ ለልብ በሽታ እና ለኩላሊት ጤና ስጋት ይሆናል።
2️⃣ ኤም.ኤስ.ጂ (MSG - Monosodium Glutamate)፡
ለጥሩ ጣዕሙ ምክንያት የሆነው ይሄ ውህድ ቢሆንም፣ አንዳንድ ሰዎች ላይ ግን ለራስ ምታት፣ ለሆድ መነፋት እና ለአለርጂ ዓይነት ስሜቶች መንስኤ ሊሆን ይችላል።
3️⃣ ሰው ሰራሽ ቅመሞች እና የተቀነባበሩ ዘይቶች፡
አብዛኞቹ ኩቦች የተቀነባበሩ ዘይቶችን እና የመጠቂያ ጊዜያቸውን የሚያራዝሙ ሰው ሰራሽ ነገሮችን ይይዛሉ።
💡 ምን ብናደርግ ይሻላል? (ጤናማ አማራጮች):
1️⃣ መጠናቸውን መቀነስ፡ ሙሉ ኩብ ከመጨመር ይልቅ ግማሹን ብቻ መጠቀም።
2️⃣. ተጨማሪ ጨው አለመጨመር፡ ምግብ ውስጥ ክኖር ካደረጉ በኋላ የገበታ ጨው መደገም የለበትም።
3️⃣. በተፈጥሯዊ ቅመሞች መተካት (በጣም የሚመከር)፡
*ሀ*. ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል፣ እርድ፣ ከሪ (Curry)፣ ኮረሪማ፣ እና ጥቁር አዝሙድ በመጠቀም ምግባችንን ማጣፈጥ።
*ለ*፡ የዶሮ ወይም የበሬ አጥንት በቤት ውስጥ አፍልቶ መረቁን (Bone Broth) ለምግብ ማጣፈጫነት መጠቀም።
🚨 ቁልፍ ማስታወሻ፡ አልፎ አልፎ በመጠኑ መጠቀም አጣዳፊ ችግር ባያመጣም፣ የደም ግፊትና የኩላሊት ህመም ያለባቸው ሰዎች ግን አጠቃቀማቸውን ቢቀንሱ ወይም በተፈጥሯዊ ቅመሞች ቢተኩ ይመከራል!
❤️ **ጤናችን በምግባችን ውስጥ ነው!**
ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ (Share)! 🔄
በለስ ጤናማ ይሆን?
#በለስ
ጤና ይስጥልኝ!
💡 "ካሎሪ ቀንሼ እያለ ክብደቴ ለምን አልቀነስ አለ?" (ከstatic Calorie Deficit or CICO ወደ Dynamic የNIH Neuro-endiocrine ሞዴል)
ብዙዎቻችን «በቀን 500 ካሎሪ ብቀንስ በሳምንት ግማሽ ኪሎ፣ በዓመት 24 ኪሎ እቀንሳለሁ» የሚለውን የቆየ የቀመር ህግ እንሰማለን። ነገር ግን በተግባር ሲሞከር የተወሰነ ቀንሰን ክብደታችን በአንድ ቦታ ይቆማል (Plateau)! ለምን ይመስላችኋል?
ምክንያቱም የሰውነታችን ሜታቦሊዝም እንደ ሂሳብ ማሰቢያ (Calculator) ቀጥተኛና ቋሚ ስላልሆነ ነው!
በአዲሱ የNIH (የአሜሪካ ብሔራዊ የጤና ተቋም) ምርምር መሠረት፡
1️⃣ ሰውነታችን ይቀየራል፡ ክብደት በሚቀንስበት ጊዜ ሰውነታችን የካሎሪ ማቃጠል አቅሙን በራሱ ይቀንሳል (Adaptive Thermogenesis)።
2️⃣ የካርቦሃይድሬት እና ኢንሱሊን ተፅዕኖ፡ ካርቦሃይድሬት የበዛበት ምግብ ስንመገብ ኢንሱሊን ይጨምራል፤ ይህ ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ ያለው ስብ እንዳይቃጠል የሆርሞን "ቁልፍ" ይዘጋበታል።
3️⃣ የርሀብ ሆርሞኖች ይነሳሉ፡ ሌፕቲን (Satiety Hormone) ሲቀንስና ግሬሊን (Hunger Hormone) ሲጨምር አእምሮአችን የረሃብ አደጋ እንደተደቀነበት በማሰብ ምግብ እንድንፈልግ ይገፋፋናል።
በአጭሩ፡ ክብደት መቀነስ ቀጥተኛ መስመር ሳይሆን የሆርሞኖች እና የሰውነታችን የተፈጥሮ መከላከያ ስርዓት ውጊያ ነው!
ይህንን ሳይንሳዊ እውነታ፣ የካሎሪ እና የሆርሞኖችን ሚስጥር እንዲሁም ለምን አትሌቶች እና ተራ ሰው የተለየ ውጤት እንደሚያዩ በጥልቀት የተተነተነበትን ሙሉ ሰነድ (Document) ማንበብ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያገኙታል👇
(በአማርኛ ከፈለጉ comment ላይ "Amharic" ብላችሁ ጠይቁኝ።)
🔗 ሙሉ ሰነዱን ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡ ወይም copy አርገው ብራውዘር ላይ paste ያርጉት፡ 👇
https://drive.google.com/file/d/1GcH1n3vgZCTLDys2XJbpZ4_C_f1w9CXU/view?usp=sharing
#ጤና #ክብደትመቀነስ #ሜታቦሊዝም #የጤናመረጃ
By Dr Markos
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
BMA Plaza/Suite 707
Addis Ababa
1000