Yeab sera medium clinic and diagnostic Laboratory

Yeab sera medium clinic and diagnostic Laboratory

Share

it is a basic medical laboratory center found in Hawassa city alamura near kerod caffe it is a pri

03/08/2026
16/06/2026

የማክሰኞ ሰይፈ ሥላሴ

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በእውነት አምናለሁ።

፩. አቤቱ በረከትህን ስጠኝ በዚች በተባረከችው ዕለት የማቀርብልህን ጸሎት ስማኝ ልመናዬን ተቀበል ኃጢአቴንም ይቅር በለኝ።
፪. አቤቱ ለሚበረታቱብኝ እጅ አሳልፈህ አትስጠኝ የሰይጣንን ተንኮል እና የባለሥልጣኖችን ቁጣ አታድርስብኝ የጐረቤትን ጥል ከኔ አርቅልኝ ሐዘንና ችግርንም ከላዬ ላይ አስወግድልኝ።
፫. አቤቱ ትእዛዝህን እፈጽም ዘንድ ዓይነ ልቡናዬን አብራልኝ መፈራትህንም በዚች በዛሬይቱ ዕለት ፈጥነህ ላክልኝ።
፬. ደጋጎች ወገኖችህን በቀንና በሌሊት እንደጠበቅሃቸው ሁሉ በደሌንና ኃጢአቴን ይቅር ትል ዘንድ በእውነተኞች ወዳጆችህ አማላጅነት (ስም) እለምንሃለሁ።
፭. አቤቱ በፊተኛውም ሆነ በኋለኛው ኃጢአቴ ማረኝ ይቅር በለኝ ከምቀኛና ከተንኮለኛ እንዲሁም በእኔ ላይ ክፉ ለማድረግ ከሚፈልጉ ሁሉ ፈጽመህ አድነኝ በአንተ እታመናለሁ አቤቱ ከአንተ ሌላ አምላክ የለምና ።
፮. አምላኬ ሆይ ስማኝ ፈቃዴንም ፈጽምልኝ ወገኖችህ የጥምቀት ልጆችንም ጠብቃቸው።
፯. ጥንት የሌለብህ ቀዳማዊ ፍጻሜ የሌለብህ ደኃራዊ ሆይ አቤቱ በደሌን ታጠፋልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ እማልድሃለሁ በአባቴና በእናቴም ላይ ፍጹም ርኅራሄ አድርገህ ከወገኖችህ ጋር በመንግሥተ ሰማያት አንድ ታደርጋቸው ዘንድ ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው።
፰. ኃይል ምስጋና ጌትነትና መንግሥት ያንተ ናትና።
፱. በእውነት የሚጠሩህን የምትሰማቸው ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ ቸርነትህንም ከኔ አታርቅ አቤቱ በቸርነትህና በይቅርታህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።
፲. ክብር ጌትነትና ምስጋና ለአንተ ይገባል ለዘለዓለሙ አሜን።
፲፩. በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ ገጽታዬን አማትባለሁ በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ በፊቴ አንፃር አማትባለሁ በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ በስተኋላዬ አማትባለሁ።
፲፪. በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ ወደ ቀኝ አማትባለሁ በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ ወደግራ አማትባለሁ በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ በመላ ሰውነቴ አማትባለሁ።
፲፫. ይልቁንም ኃጥእና በደለኛ የምሆን በዚህ ዓለም በሕይወት በምኖርበትና ከሞትኩም በኋላ በሚመጣው ዓለም ርኵሳን መናፍስት እንዳይቀርቡኝና እንዳይፈታተኑኝ እግሮቼንና እጆቼን መቀመጫና መቆሚያዬን መውጫና መግቢያዬን ሁሉ በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ አማትባለሁ።
፲፬. አንድ ሲሆን ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ ለሚሆን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ፤ በዚህም ሥላሴ በገጽ ሦስት በመለኮት አንድ መሆናቸው ይታወቃል።
፲፭. በገጽ ሦስት ስለመሆናቸው ሦስት በመለኮት ትክክል ስለመሆናቸው አንድ ይባላል።
፲፮. ልዩ ሦስት የሚሆኑ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአነዋወር ትክክል በመሆናቸው አንድ እግዚአብሔር እንላለን።
፲፯. በስም በአካል ሦስት ቢሆን በአገዛዝ በፍርድ አንድ ነው ጥበቡ ምክሩ የማይከፋፈል የማይነጣጠል ፍጹም አንድ ነው።
፲፰. አብ ያለወልድና ያለመንፈስ ቅዱስ ለብቻው አያስብም።
፲፱. ወልድም ያለአብና ያለ መንፈስ ቅዱስ ብቻውን አያስብም።
፳. መንፈስ ቅዱስም ያለአብና ያለወልድ ብቻውን አያስብም።
፳፩. እነሱስ ያለመለየት በአንድ ሐሳብ ጸንተው ይኖራሉ።
፳፪. ሥላሴ በአካል ሦስት በሥልጣን አንድ ናቸው።
፳፫. አብ በተለየ አካሉ ፍጹም ገጽ አለው በባሕርይ ግን ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አንድ ነው።
፳፬. ወልድም በተለየ አካሉ ፍጹም ገጽ አለው በባሕርይ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አንድ ነው።
፳፭. መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ ፍጹም ገጽ አለው በባሕርይ ግን ከአብ ከወልድ ጋራ አንድ ነው።
፳፮. አብ በተለየ ስሙ አብ ሲሆን መለኮቱ ግን ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ አይለይም።
፳፯. ወልድም በተለየ ስሙ ወልድ ሲሆን መለኮቱ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አይለይም።
፳፰. መንፈስ ቅዱስም በተለየ ስሙ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን መለኮቱ ግን ከአብ ከወልድ አይለይም።
፳፱. የአብ ስም ተለውጦ ወልድ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም በመለኮቱ ግን ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፴. የወልድ ስሙ ተለውጦ አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም በመንግሥቱ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አንድ ነው።
፴፩. የመንፈስ ቅዱስ ስም ተለውጦ አብ ወይም ወልድ አይባልም የመለኮቱ ፈቃድ ግን ከአብ ከወልድ ጋራ አንድ ነው።
፴፪. አብ አባት በመሆኑ ከባሕርይ ልጁ ከወልድ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስም አይበልጥም።
፴፫. ወልድም ከአባቱ አያንስም ከባሕርይ አባቱና ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ አነዋወር ነው እንጂ።
፴፬. መንፈስ ቅዱስም ያለመጉደልና ያለመበላለጥ ከአብና ከወልድ ጋር በምክርና በአነዋወርም ትክክል ያለመለየት በጥበብ አንድ ናቸው።
፴፭. በመንግሥት ትክክል በአካል ሦስት በመለኮት አንድ ናቸው።
፴፮. የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ሦስትነታቸውና አንድነታቸው እንደዚህ ነው። ሦስትነታቸው በትጉሃን መላእክት ምስጋና ይታወቃል።
፴፰. ኪሩቤልና ሱራፌል ሊቃናትም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር የአማልክቶች አምላክ እርሱ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ መመስገን ይገባዋል እያሉ በአንድ ቃል ያመሰግኑታል።
፴፱. በዚህም ምስጋና አርባዕቱ እንስሳ ለአምላክነቱ በመገዛት በአንድነት ሥላሴን ያመሰግናሉ።
፵. መንፈሳውያን የሆኑ ሱራፌልም ሦስትነቱንና አንድነቱን ለማጠየቅ አሸናፊ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ ትመሰገናለህ የጌትነትህም ምስጋና በሰማይና በምድር የመላ ነው እያሉ ኃይል ገንዘቡ ለሚሆን አምላክ ምስጋና ያቀርባሉ።
፵፩. በዚህ የምስጋና ቃል የሥላሴ አነዋወር ይታወቃል እነሆ ለሦስትነቱ ምስጋና በሚያቀርቡበት ጊዜ ቅዱስ ብሎ ማመስገን ከሦስትነት አይወርድም አይወጣምና።
፵፪. አኛም እንደዚሁ መለኮተ ሥላሴን እናመሰግናለን የተመሰገነ አብ ልዑል ነው የተመሰገነ ወልድም ክቡር ነው የተመሰገነ መንፈስ ቅዱስም ታላቅ ነው እያልን ልዩ ሦስት ለሚሆን እንሰግዳለን።
፵፫. በሦስትነቱ ፈጽመን እናመልክበታለን እሱንም እናመሰግነዋለን ለዘለዓለሙ በእውነት።
፵፬. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በገጽ ሦስት በባሕርይ አንድ ናቸው በስም ሦስት በመንግሥት ትክክል በአካል ሦስት በመለኮት በችሎታ ሁሉ አንድ ናቸው።
፵፭. ሦስት ፀሐይ አንድ ብርሃን ሦስት ገጽ አንድ አምላክ ከፍጹም ሦስትነት ባለመለየት አንድ ቃል አንድ መለኮት ነው።
፵፮. አብ በሚናገርበት ገንዘብ እሱ ወልድ መንፈስ ቅዱስም በአንድነት ይናገራሉ።
፵፯. አብ በባሕርይ ልጁ በወልድ በባሕርይ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ አንድነት ይናገራል።
፵፰. ወልድም በባሕርይ አባቱ በአብ በባሕርይ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ አንድነት ይናገራል።
፵፱. መንፈስ ቅዱስም በአብ በወልድ አንድነት ይናገራል።
፶. የአብ ቃል ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፶፩. የወልድም ነገር ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፶፪. የመንፈስ ቅዱስም ነገር ከአብ ከወልድ ጋር አንድ ነው።
፶፫. አብ በሚናገርበት ገንዘብ እርሱ ወልድ በአብ ይናገራል።
፶፬. ወልድም በሚናገርበት ገንዘብ እርሱ አብ በወልድ ይናገራል።
፶፭. የመንፈስ ቅዱስም ነገር ከአብ ከወልድ ነገር ጋር አንድ ነው፤ እሱ በፍጹም አካሉ አምላክ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ የአብ የወልድ የባሕርይ ሕይወት ወይም እስትንፋስ ነው ተብሎ እንደተነገረ መንግሥቱ ከአብ ከወልድ አይለይምና።
፶፮. ወልድም እንደዚሁ እንደ አብና እንደ መንፈስ ቅዱስ ፍጹም ገጽ ሲኖረው በመለኮቱ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነውና።
፶፯. እርሱ ቃል (ወልድ) እኔ በአብ አብም በእኔ ህልዋን ሆነን እንኖራለን ብሎ እንደተናገረ እርሱ የአብ ቃል ይባላል።
፶፰. እንደዚሁ በአንድ ቃል ሦስት ነገር (አካል) እንዳለ እናምናለን አስቀድሞ ወንጌላዊው ዮሐንስ እንደ መሰከረ እንዲህ ሲል።
፶፱· ቃል አስቀድም ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
፷· ይህም አስቀድሞ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
፷፩. ሁሉም በእርሱ ሆነ ከሆነውም ሁሉ ያለእርሱ ምንም ምን የሆነ የለም።
፷፪. ሕይወት በእርሱ ነበረች ያችም ሕይወት የሰው ልጅ ብርሃን ነበረች።
፷፫. ብርሃኑም በጨለማ ያበራል ጨለማም አላገኘውም አይቀርበውምም።
፷፬. ይህ ብሩክ ቃል ቡርክት ለሆነች ለማርያም በመልአኩ በገብርኤል አምሣል እንደተገለጸላት ለኔም እንዲሁ ተገልጻችሁልኝ የሕይወት ቃል አሰሙኝ።
፷፭. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት በመለኮት አንድ ናቸው ከዚህ አይወጡም ወይም አይወርዱም።
፷፮. ከዚህ አይበልጡም ወይም አይጐድሉም ጉድለት ወይም ተጨማሪ አይስማማቸውምና።
፷፯. በአንድ ይሰገዳሉ በገጽ ሦስት በመለኮት አንድ ናቸው ቅድመ ዓለም ያለመጉደል በአንድነታቸውና በሦስትነታቸው ጸንተው የነበሩ ናቸው።
፷፰. አብ አባት በመሆን ከወልድ አይቀድምም ወልድም ልጅ በመሆን ተድኅሮ የለበትም መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ቅድምና ወይም ተድኅሮ የለበትም።
፷፱. ከዓለሙ ሁሉ በፊት በአንድ አገዛዝ በአንድ ሥልጣን በሦስትነታቸው የነበሩ ናቸው።
፸. መለኮትነታቸውን አስቦ ለመናገር የህልውናቸውንም ጥልቀት ለመመርመር ፈጽሞ አይቻልም ጥንት የሌለበት የመኖር ቅድምና ባለቤት ናቸው እንጂ።
፸፩. ያለምንም መለየት ወይም ልዩነት በሦስትነታቸው ያሉ ናቸው። ያለምንም መጉደል በትክክል ለዘለዓለሙ የሚኖሩ ናቸው።
፸፪. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ዙፋን ይቀመጣሉ (ህልዋን ናቸው) የአብ ህልውና ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ህልውና አይለይም የወልድም ህልውና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ህልውና አይለይም የመንፈስ ቅዱስም ህልውና ከአብ ከወልድ ህልውና አይለይም።
፸፫. አብ በፍጹም አካሉ ህልው ነው ነገር ግን አርአያ መለኮቱ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ አርአያ መለኮት የተለየ አይደለም።
፸፬. ወልድም በፍጹም አካሉ በአብ ቀኝ ህልው ነው ነገር ግን ሥነ መለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሥነ መለኮት አይለወጥም።
፸፭. መንፈስ ቅዱስም በፍጹም አካሉ በአብና በወልድ ቀኝ ህልው ነው ነገር ግን ሕብረ መለኮቱ ከአብና ከወልድ ሕብረ መለኮት አይለይም።
፸፮. እንግዲህ የሥላሴ በአንድ የጌትነት ዙፋን አነዋወራቸው ይህ ነው ነቢዩ እንደተናገረ እንዲህ ሲል።
፸፯. እንደመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ ብሎ ጌታ ጌታዬን በቀኜ ተቀመጥ አለው።
፸፰. እነሆ ልዩ ሦስት የሚሆን የሥላሴን የአንድነት አነዋወር በየክፍሉ ተረዳን።
፸፱. በዚህ በቅድስት ሥላሴ አነዋወር እኔ አገልጋያችሁ . . . እማፀናለሁ ነፍሴና ሥጋዬንም አማፅናለሁ ልዩ ሦስት የሚሆን እሱ በማይደርቅ የቸርነቱ ባሕርይ በየጊዜውና በየሰዓቱ ያጠምቀኝ ዘንድ ለዘለዓለሙ አሜን።

ተአምር፦
፩. ይቅርታቸው ሀብተ ረድኤታቸው በወዳጃቸው በ . . . ላይ ይደርና የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተአምራቸው ይህ ነው።
፪. የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስን መታሰቢያ የምታደርግ ልጅ የሆነ አንድ ሕፃን ነበር።
፫. ከዕለታት በአንደኛው ቀን ይህቺ ሴት ለሥላሴ መታሰቢያ እንጀራ የምትጋግርበት ደረቅ እንጨት ፈልጋ ባጣች ጊዜ ያን ሕፃን ልጅዋን ውድ ልጄ ሆይ ባደግህ ጊዜ የምትከፍለው ደረቅ እንጨት የሚሰጥህ ሰው ፈልግ እኔ እንጨት በመፈለግ ብዙ ደክሜ አጥቻለሁና አለችው።
፬. ሕፃኑም መልሶ መልካሟ እናቴ ሆይ ሁሉንም ነገር ተይው ይቅር ብዙውን አትድከሚ ነገር ግን ጌቶቻችን ሥላሴ ያውቁልናል አላት።
፭. ይህን ከተባባሉ በኋላ ዳግመኛ እናቱን ጠራትና አስኪ ተነሽና የመጣልሽን ደስታ ተመልከች አላት።
፮. ልቡሳነ መብረቅ በሆኑ መላእክት እጅ የተዘጋጀ እንጂ በሰው እጅ የተጋገረ ያይደለ የትኩስ እንጀራ መዓዛ ሽታ በዚህ አዳራሽ ውስጥ ይሸታልና አላት።
፯. ይህንንም በሰማች ጊዜ ፈጥና ወደ ቤት ገባችና መዓዛው ሽታው ወይም የሰውን ልብ እጅግ አድርጎ የሚመስጥና የሚያስደስት እንጀራ በመሶብና በገበታ ተሠርቶ አገኘች። ሰዎችም ከመዓዛው ጣፋጭነት የተነሣ በሽታው ብቻ እንደበሉ ሆነው ጠገቡ።
፰. በዚህም ጊዜ ዘመዶችዋንና ጐረቤቶችዋን ጠርታ ወዳጆቼ ሆይ በቤቴ ውስጥ የሆነውን ማለት ሥላሴ ያደረጉትን ድንቅ ድንቅ ሥራ ኑና ተመልከቱ አለቻቸው።
፱. የሀገሩም ሰዎች ለደጋጐች ወዳጆች የሆኑ እሊህ ሥሉስ ቅዱስ ያደረጉትን ድንቅ ሥራ ተመልክተው አደነቁ በታላቅ ደስታም እየተደሰቱ በአንድነት ወደ አዳራሹ ገቡ።
፲. ከዚህ በኋላ የሀገሩ ሰዎች ሁሉ ሥሉስ ቅዱስ ሰዶምና ገሞራን ያጠፉበትን ጥር ፯ (7) ቀን ምክንያት በማድረግ እንደዚች ሴት ሁሉም በየራሳቸው የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን መታሰቢያ ማድረግ ጀመሩ።
፲፩. እነሆ ነዳያንና ችግረኞችን እየጠሩ ከተዘጋጀው ምግብ አብልተው አጠገቧቸው ወይንና ብርዝም አጠጥተው አረኳቸው ወደ እነሱ የመጡትን ሁሉ በእርጋታ እየጋበዙ አስደሰቷቸው።
፲፪. በየወሩ ሁሉ በየራሳቸውና በየግል ቤታቸው የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስን የበዓላቸውን መታሰቢያ የሚያደርጉ ሆኑ ይልቁንም በጥርና በሐምሌ ፯ ቀን ያለማጓደል በፍጹም ትጋት ይዘክሩ ጀመር።
፲፫. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው ከወዳጃቸው . . . ጋር ለዘላለም ይኑር አሜን።

Photos from Yeab sera medium clinic and diagnostic Laboratory's post 16/04/2026
Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa