Abey_Peres

Abey_Peres

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abey_Peres, Health/Beauty, Addise, Addis Ababa.

Photos from Abey_Peres's post 25/07/2026

በቅድመ ጎርፍ መካከል ስራ ከ229 ሺህ በላይ ሰዎችን ከመፈናቀል ማዳን ተችሏል
+++++++++++

በጎርፍ ተጋላጭነታቸው ቅድሚያ በተሰጣቸው አካባቢዎች በተሰራው የቅድመ ጎርፍ መከላከል ስራ ከ229 ሽህ በላይ ሰዎችን ከመፈናቀል ማዳን መቻሉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከተጠሪ ተቋማትና ከክልሎች ውሃና ኢነርጂ ቢሮዎች ጋር የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ እንደገለጹት፤ በጎርፍ ተጋላጭነታቸው ቅድሚያ በተሰጣቸው ተፋሰሶች አካባቢ 255 ነጥብ 65 ኪሎ ሜትር የሚደርስ የቅድመ ጎርፍ መከላከል ሥራ ተሰርቷል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት ይከሰት የነበረው የጎርፍ አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል።

የጎርፍ መከላከል ሂደቱ በአዋሽ ተፋሰስና በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች አካባቢ የተተገበሩ ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ፤ በዚህም 70 ሺህ 140 ሄክታር የእርሻ ማሳና 229 ሺህ 189 ሰዎችን ከመፈናቀልና ከጉዳት መከላከል መቻሉን ጠቁመዋል።

በሁሉም ክልሎች በሚባል ደረጃ ቅንጅታዊ አሰራር እውን ማድረግ መቻሉን በመግለጽ፤ በክልሎች መካከል ያለው የንጹህ መጠጥ ውሃ የተደራሽነት ልዩነት ለማጥበብ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።

በሀገሪቱ አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን 75 ነጥብ 59 በመቶ ደርሷል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የገጠርና ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋንን ለማሳደግ በትኩረት መሰራቱንም አብራርተዋል፡፡

በዚህም አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥር ከ84 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ መድረሱን አስረድተዋል፡፡

20/07/2026

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አሶሳ ከተማ በተደረገው የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም የግምገማ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይበውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ርሡልጣን ወሊ የተደረገ የመክፈቻ ንግግር

15/07/2026

ሀገሬ እንድናገር ጠርታኛለች

Photos from Abey_Peres's post 12/07/2026

⚡️ ( ) !
ለአራት ቀናት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ሲካሄድ የቆየው 22ኛው የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር (EAPP) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጉባኤ ስኬታማ ውይይቶችን በማድረግ ተጠናቋል።
በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ኢትዮጵያ የቀጣናውን የኃይል ትስስር በሊቀመንበርነት የመምራት ኃላፊነቱን ከግብፅ በይፋ ተረክባለች።
📌
• የሊቀመንበርነት ሽግግር፦ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት ዘመኗ የቀጣናውን የኤሌክትሪክ ግብይት ለማስፋፋት እና ታዳሽ ኃይልን ለማበረታታት ከአባል ሀገራት ጋር በቅርበት ትሰራለች።
• ፦ በጉባኤው ከፍተኛ ትኩረት ያገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ገበያ ማዕከል ዋና መቀመጫን የመወሰን ጉዳይ ነበር። ከአስተናጋጅ ሀገር ምርጫ ጋር ተያይዞ ከግብፅ ጋር የነበሩ አለመግባባቶችን በድርድርና በጋራ መግባባት ለመፍታት ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
• ፦ የ37ኛው የስቲሪንግ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ፤ የተቋማዊ አሰራር ማሻሻያዎችን፣ የህግ ማዕቀፎችን ማጠናከር እና የክልላዊ የኃይል ገበያ ልማት ዕቅዶችን በጋራ አፅድቀዋል።
፦ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር (EAPP) 13 አባል ሀገራትን ያቀፈ ተቋም ሲሆን፤ ዋና ዓላማው የኤሌክትሪክ አቅርቦትን በማስተሳሰር የኃይል ደህንነትን ማረጋገጥ፣ ወጪን መቀነስ እና ቀጣናዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ማሳደግ ነው።

Photos from Abey_Peres's post 08/07/2026

⚡️ (Day-Ahead Market) #በአስቸኳይ !
በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 37ኛው ልዩ የምስራቅ አፍሪካ ኃይል ትስስር (EAPP) የስቲሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ፣ ኢትዮጵያ የቀጠናዊ የኤሌክትሪክ ገበያ (Day-Ahead Market - DAM) በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገባ ጠንካራ ጥሪ አቅርባለች።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ እና የኮሚቴው ሰብሳቢና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ላይ የተላለፉ ዋና ዋና መልዕክቶች፡-
• 🛑 የገበያው መዘግየት ጉዳት፡ የገበያው መዘግየት አባል ሀገራት ከድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ንግድ ሊያገኙ የሚችሉትን ከፍተኛ የኢኮኖሚና የልማት ጥቅሞች እያሳጣ መሆኑ ተገልጿል።
• 💡 የቴክኒክ ዝግጁነት፡ ለገበያው መጀመር የሚያስፈልጉ የቴክኒክ ዝግጅቶች እና የንግድ መድረክ ፍተሻዎች ከአንድ ዓመት በፊት ቢጠናቀቁም፣ በአባል ሀገራቱ የአስተዳደር ማሻሻያ ስምምነቶች መጓተት ምክንያት እስካሁን ወደ ሥራ አልገባም።
• 🤝 የኢትዮጵያ አማራጭ ሀሳብ፡ በአስተዳደር ማዕቀፎች (IGMOU እና IUMOU) ላይ የሚደረጉ የማሻሻያ ውይይቶች ጎን ለጎን እየቀጠሉ፣ የኤሌክትሪክ ገበያው በአሁኑ አወቃቀር ስር በአስቸኳይ ሥራ እንዲጀምር ኢትዮጵያ አሳስባለች።
• 🌍 ቀጣይ እርምጃ፡ በስቲሪንግ ኮሚቴው የሚዘጋጁት የውሳኔ ምክረ-ሀሳቦች ከሐምሌ 3 እና 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሚካሄደው 22ኛው ልዩ የEAPP የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ለውሳኔ ይቀርባሉ።
ምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ የኢነርጂ ሀብት ቢኖራትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች አሁንም የኃይል አቅርቦት ያጥራቸዋል። ይህንን ችግር ለመቅረፍና ቀጠናዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን የኃይል ትስስሩን በተግባር ማስጀመር ወሳኝ መሆኑ ተረጋግጧል።

06/07/2026

"Energy is the driver of economic growth." — H.E. Dr. Eng. Sultan Wali, State Minister for Energy Development, Ministry of Water and Energy.

22/06/2026

survive ለማድረግ ደግሞ መደመር አለብን

Photos from Mayor Office of Addis Ababa's post 14/06/2026
Photos from Abey_Peres's post 05/01/2026

የ7/24 ተግባር በለውጥ ጎዳና:-

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addise
Addis Ababa