Etcare
An official page of Etcare! Etcare is a Direct and Network Marketing company that produces and sells skin and personal care products!
26/09/2026
በኢቲኬር የተዘጋጀው ግራንድ ቢኦፒ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታዳሚዎች በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል።
በልዩ አቀራረብ የምርትና ቢዝነስ ገለጻ የሰጡት፡ የኢቲኬር ኤክፐርት አሰልጣኝ በእምነት አበበ ፣ ኤክስፐርት አሰልጣኝ ኤፍሬም ተፈራ እና የኢቲኬር ማናጀር አበበች ሲመል ሲሆኑ፣ መድረኩን በስኬት የመራው የኢቲኬር ሊደር እንዳወቅክ አያሌው ነው።
26/09/2026
እንኳን አደረሳችሁ!
ልዩ የመስቀል በአል መዳረሻ ፕሮሞሽን ከኢቲኬር ለኢቲኬሪያንስ
ሰኞ መስከረም 18
ለ 1 ቀን የሚቆይ ታላቅ የምርት ሽያጭ ፕሮሞሽን።
በሁሉም የኢቲኬር ቅርንጫፎች Buy 2 Get 1 Free promotion ተግባራዊ ይሆናል።
ሰኞ መስከረም 18 ብቻ ስለሆነ ለስጦታዎ ይዘጋጁ!
ተጨማሪ ማብራሪያዎችን በአቅራቢያዎ በሚገኙ ቅርንጫፎች ማግኘት ይችላሉ።
Etcare
26/09/2026
እንኳን ለመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ!
ኢቲኬር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የምርት አስተዋዋቂዎች ፣ ደንበኞች እና ሰራተኞች እንኳን ለመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
መልካም በአል
25/09/2026
የነገ ተስፋን አብረን እንገንባ፡ የኢቲኬር የመሪዎች ቡድን ለእዝነት የሰረብራል ፓልሲ መርጃ ድርጅት ድጋፍ አደረገ!
የኢቲኬር ሊድ ቲም እና የአዲስ አበባ አሶሺየት ቲም "ለሲፒ ጉዳተኞች የነገ ተስፋ እጓዛለሁ" በሚል መሪ ቃል ለተዘጋጀው የእግር ጉዞ T-shirt በመግዛት ለእዝነት የሰረብራል ፓልሲ ጉዳተኛ ህፃናት እና ወላጆች መርጃ በኢትዮጵያ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።
ጥቅምት 8 በሚካሄደው በዚህ በጎ አድራጎት ላይ በመሳተፍ ለህፃናቱ እና ለወላጆቻቸው ተስፋንና ድጋፍን ለማበርከት የተቻለ ሲሆን፣ ሁላችንም እንደ ኢቲኬሪያንስ በማህበራዊ ኃላፊነታችን ግንባር ቀደም ልንሆን ይገባል!
ድርጅቱን ለመጎብኘት ወይም ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ:
አድራሻ: አዲስ አበባ — ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ፣ ከ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ አለፍ ብሎ፣ ከውሃ ልማት ፊት ለፊት ባለው ቅያስ 40 ሜትር ገባ ብሎ (ከፒያሳ ሆቴል ፊት ለፊት)።
የድርጅታችንን እሴት በተግባር ላሳዩት መሪዎቻችን እና የቡድን አባላቶቻችን ምስጋናችን የላቀ ነው!
Etcare
25/09/2026
ኢቲኬር ግራንድ ቢኦፒ በቅዳሜ ቀን 16/01/2019 አ.ም
በነገው እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ጀምሮ ግራንድ ቢኦፒ በኢትኬር ዋና መስሪያ ቤት የሚሰጥ ሲሆን ስለ etcare ምንነት፣ የአሰራር ሂደት፣ስለ ምርቶቹ እና የክፍያ መንገዶች ገለፃ የሚሰጥበት የኢቲኬር ግራንድ ቢኦፒ በድምቀት ይከናወናል።
የነገውን ገለፃ የኢቲኬር ኤክስፐርት ትሬነር በእምነት አበበ ፣ የኢቲኬር ኤክስፐርት ትሬነር ኤፍሬም ተፈራ እና የኢቲኬር ማናጀር አበበች ሲመል የሚሰጥ ሲሆን ፣ የኢቲኬር ሊደር እንዳወቀ አያሌው ደግሞ መድረኩን ይመራዋል።
Etcare
25/09/2026
ዋሴ ደሞዜ(ኢቲኬር ማናጀር)
ይህ የስኬት ሽግግር ፣ የበለጠ የስራ ተነሳሽነቶን የሚያስቀጥሉበት እና በአስደናቂ ስኬቶችዎ ሌሎችን ማበርታትዎን ካለፈው በላቀ ሁኔታ የሚቀጥሉበት እንደሚሆን እናምናለን ። የእርስዎ ስኬት በትጋት፣ በፍላጎት እና በማያወላውል ቁርጠኝነት ምን ሊሳካ እንደሚችል አንጸባራቂ ምሳሌ ይሆናል፡፡ እንኳን ደስ አልዎት።
ኢቲኬር
Etcare
24/09/2026
https://youtu.be/X6MXb_q6Hrg?si=f78TxnO4mZa_usHO
የድሬዳዋ እና የሐረር ሙሉ ጉዞ ማስታወሻ! ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ያደረግነውን ሙሉ ጉዞ! ከድሬዳዋ ሞቅ ያለ አቀባበል እና አስደሳች ድባብ ጀምሮ፣ በታ...
24/09/2026
"Unlocking Life Skills for Success!”
የኢቲኬር የህይወት ክህሎት ስልጠና መድረክ በስኬት ተከናወነ!
በዛሬው የስልጠና መድረክ የኒውሮሊንጉስቲክስ ፕሮግራሚንግ ባለሙያ ከሆነው ከ አሰልጣኝ ዳንኤል አያሌው ጋር በነበረዉ የተለየ ስልጠና እንዲሁም መድረኩን ሲመራልን የነበረው የኢቲኬር የሊድ ቲም አባልና ኤክስፐርት አሰልጣኝ የሆነዉ አብርሃም ቢራራ አማካኝነት መድረኩ በስኬት ተጠናቋል።
24/09/2026
ወደ ድሬዳዋ እና ሐረር ያደረግነው ጉዞ ሲታወስ...
የድሬን ልዩ ሞቅታ እና ድባብ አጣጥመን፣ በሐረር ደግሞ ጭልፊቶችን በእጃችን፣ ጅቦችን ደግሞ ፍርሃትን ወደጎን ትተን በአፋችን መግበን የተመለስንበት ልዩ የማይረሳ ትዝታ!
24/09/2026
የቆዳዎን ጤንነት በሼባ ሳሙና ይጠብቁ!
ከቀርከሃ ከሰል እና ከኮኮናት ዘይት የተሰራ ልዩ የetcare ምርት።
ለንጹህ እና ላማረ ቆዳ ዛሬውኑ ይሞክሩት!
Etcare
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Https://maps. App. Goo. Gl/9awY8x3TpHfJixMi 9
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 07:00 |
| Tuesday | 08:00 - 13:00 |
| Wednesday | 08:00 - 13:00 |
| Friday | 08:00 - 13:00 |
| Sunday | 08:00 - 13:00 |