Feker Engida

Feker Engida

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Feker Engida, Health/Beauty, Addis Ababa.

22/09/2026

💥እውነተኛ የፖለቲካ ጥምረት ማለት ተዋናዮች የጋራ ራዕይ ሰንቀው በህዝብ ፊት እውነትን የሚተገብሩበት ታላቅ መድረክ ነው። አሁን የተመለከትነው የጥምረት ዜና ግን፣ አዘጋጆቹ በሌሎች ስም የውሸት ማስታወቂያ አሳትመው ህዝብን የጠሩበት ርካሽ ድራማ ሆኖ አልፏል። የሴራው ጠንሳሾች ከእነዚህ ግዙፍ ኃይሎች ጋር ተጣምረናል፣ መድረኩንም በጋራ ተቆጣጥረናል ብለው ለህዝቡ ትልቅ የተስፋ ፖስተር አሳዩ። ይሁን እንጂ መጋረጃው ተገልጦ ህዝቡ ትዕይንቱን ሊያይ ሲጠብቅ፣ ዋነኛ ተዋናይ ተደርጎ ስሙ የተለጠፈው ብቅ ብሎ በዚህ ድራማ ውስጥ የለሁበትም፤ ስሜም ያለእውቅናዬ የተለጠፈ ነው በማለት የውሸት ትርክቱን እራቁቱን አስቀረው። የሌሎችን ማንነት ጠልፎ እና ያልተፈረመበትን የውሸት ስክሪፕት አንግቦ መድረክ ላይ የሚወጣ የፖለቲካ ስብስብ፣ መጨረሻው መጋረጃው ሳይዘጋ በህዝብ መሳለቂያ ሆኖ መውረድ ብቻ ነው።

07/09/2026

⌛️የህወሓት የፖለቲካ ጉዞ በአሁኑ ወቅት እጅግ አሳሳቢ እና ውስብስብ ወደሆነ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። በዋናነት ከፌደራል መንግስት ጋር የተፈረመው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በከፍተኛ ፈተና ውስጥ መውደቁ የችግሩ ማዕከል ነው።

👉የውስጥ ምንጮች እንደሚጠቁሙት፣ አዳዲስ ግጭቶችን ለመቀስቀስ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አደራዳሪ አካላትን፣ በተለይም አሜሪካን ክፉኛ አስቆጥተዋል።የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አቋም ግልፅ እና የማያሻማ ነው፤ በምስራቅ አፍሪካ ለሚፈጠረው ማንኛውም አዲስ የፀጥታ ቀውስ እና አለመረጋጋት ቀዳሚ ተጠያቂ የሚሆነው ህወሓት ነው።

✅ ይህ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ የድርጅቱን ቀጣይ እርምጃዎች በእጅጉ የገደበው ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን የፖለቲካ ተፅዕኖ በነፃነት እንዳያራምድ ትልቅ እንቅፋት ፈጥሮበታል።

07/09/2026

ለህወሓት አመራሮች የመጨረሻው የጥፋት ደወል ተደውሏል፤ መቃብራችሁም በአፍጢሙ ተደቅኗል! የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሳችሁ ለመንፈራገጥ የምታደርጉት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰይፍ አንገታችሁን ያስቀላል። አሜሪካና ትራምፕ በምስራቅ አፍሪካ ለምትጭሩት ለማንኛውም እሳት 'አንደኛ ተጠያቂ' አድርገው ፈርጀው ጨርሰውላችኋል። በውስጣችሁ ያለው መከፋፈል እንደ ምስጥ እየበላችሁ፣ በውጭ ያለው ማዕቀብና የሽብርተኝነት ፍረጃ ደግሞ እንደ ሰንሰለት እያነቀችሁ ነው። አሁን ምርጫችሁ ሁለት ብቻ ነው፡ ወይ በሰላም እጃችሁን ሰጥታችሁ ወደ ታሪክ ቆሻሻ መጣያ መውረድ፣ ወይም ደግሞ በትራምፕና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ብርቱ ክንድ ተቀጥቅጦ መቃብር መግባት። ለማምለጥ የምታደርጉት ሙከራ ሁሉ የመቃብራችሁን ጉድጓድ ያጠልቀዋል እንጂ አያድናችሁም! የታሪክ ፍጻሜያችሁ ላይ ቆማችኋል!

06/09/2026

ጳጉሜ 1 — የእምርታ ቀን! 🏭⚙️🇪🇹
«ኢትዮጵያ ታመርት» ንቅናቄ አዳዲስ ፋብሪካዎችን በመክፈት የኢንዱስትሪ እምርታ አምጥቷል። የውጭ ምርት ጥገኝነትን በመቀነስ ለብዙ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፤ ‘Made in Ethiopia’ ምርቶችም ለአለም ገበያ እየቀረቡ ነው
መልካም የምርታማነት ቀን! 🇪🇹💪
#ጳጉሜ1
#የምርታማነትእናየእምርታቀን
#ኢትዮጵያታመርት

06/09/2026

ከታሪካዊ የድንበር ማስከበር ተጋድሎ እስከ ዘመናዊው የምግብና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት! አባቶቻችን በደምና በአጥንታቸው ያቆዩልንን ሀገር፣ ዛሬ በላባችንና በሥራችን እውነተኛ ነጻነቷን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከስንዴ ገዢነት ወደ አፍሪካ ቀዳሚ አምራችነት የተደረገው ሽግግር፣ በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን ማረጋገጣችን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» የኢንዱስትሪ ህዳሴ እና የድፍረት የተሞላው የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም የእመርታ ጉዟችን ማሳያዎች ናቸው። በፅናትና በቁርጠኝነት ወደ ታላቅ ከፍታ!
#የእመርታቀን
#ኢትዮጵያታምርት
#ሌማትትሩፋት
#የኢኮኖሚሉዓላዊነት
#የስንዴምርታማነት
#የምግብዋስትና

22/06/2026

🇪🇹✨እግር ጥሎት ሳይሆን ራዕይ መርቶት፣ ብርድና ድካምን በሀገራዊ ፍቅር እያሸነፈ ለ24 ሰዓታት በዲሲፕሊን የተሰለፈው አስተዋይ ሕዝባችን ዛሬ የሉዓላዊነታችንን ማኅተም አትሟል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስተላለፈው ይፋዊ መግለጫ መሠረት ብልፅግና ፓርቲ 438 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን በብቸኝነት በማሸነፍ ፍፁም አብላጫ ድምፅ አግኝቷል፤ ይህ ታሪካዊ ድል እኛን ለመረጡን ብቻ ሳይሆን ካርዳቸውን በመንፈግም ቢሆን ሂደቱ ሰላማዊና ሕጋዊ እንዲሆን የሀገር ፍቅር አደራቸውን ለተወጡ ዜጎች ሁሉ የሚቀርብ ጥልቅ አክብሮትና ምስጋና ነው።

✍️አደራው ከባድ ነው፤ በትከሻችን ላይ የጫናችሁትን ታላቅ ሕዝባዊ ኃላፊነት በታላቅ ትሕትና እንቀበላለን። ፍፁም አብላጫ ድምፅ ማግኘታችን የክብር መቆናጠጫ ሳይሆን ሕዝብን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገያ ታላቅ አደራ በመሆኑ ጉድለቶቻችንን እያረምን ቃልን በተግባር በማረጋገጥ የኢትዮጵያን ከፍታ የምናበስርበት አዲስ ምዕራፍ ዛሬ ተጀምሯል!

22/06/2026

ውድ ኢትዮጵያውያን፣ ዛሬ የድሉ እውነተኛ ባለቤት እናንተ መሆናችሁን ለዓለም አሳይታችኋል! 🇪🇹 የሰጣችሁንን የ5 ዓመት አደራ የምንወጣው በንግግር ሳይሆን በተግባርና በላብ ነው:: 💪 ፊታችንን ወደ ስራ፣ ልባችንን ወደ አንድነት አድርገን ኢትዮጵያን የሁላችንም ኩራት እናደርጋታለን:: 🌟 ጉዟችን ረጅም ቢሆንም፣ የእናንተ ብርታት ለኛ ትልቅ ሞተር ነው:: ትናንትን አሸንፈናል፣ ነገንም በጋራ እንገነባለን! አብረን እንቀጥላለን፣ አብረን እናሸንፋለን! 🙏✨🤝

Category

Website

Address

Addis Ababa