bruk
rapid updet
20/01/2026
የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ኦዌን ሃርግረፍስ 45 ተኛ አመት የልደት በዓሉን እያከበረ ይገኛል
🏆 x4 ቦንደስሊጋ
🏆 x3 ዲፍቢ ፖካል
🏆 x2 ቻምፒዮንስ ሊግ
🏆 x1 ኢንተርኮንቲነንታል ካፕ
🏆 x1 ፕሪምየር ሊግ
✨🏴
20/01/2026
🇪🇺ዛሬ የሚደረጉ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች
12:30 | ካይራት አልማቲ ከ ክለብ ብሩጅ
02:45 | ቦዶ ከ ማን ሲቲ
02:45 | ኮፐንሀገን ከ ናፖሊ
05:00 | ኢንተር ሚላን ከ አርሰናል
05:00 | ኦሎምፒያኮስ ከ ባየር ሌቨርኩሰን
05:00 | ሪያል ማድሪድ ከ ሞናኮ
05:00 | ስፖርቲንግ ከ ፒኤስጂ
05:00 | ቶተንሀም ከ ዶርትሙንድ
05:00 | ቪያሪያል ከ አያክስ
19/01/2026
ብሩኖ ፈርናንዴዝ በፕሪሚየር ሊጉ የፔፕ ጋርዲዮላው ማንቸስተር ሲቲ ላይ አራት ትላልቅ የግብ እድሎችን የፈጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
Magnifico🪄
19/01/2026
ኮቢ ማይኖ አሁን ላይ በማይክል ካሪክ እምነት ከተጣለበት ቡሃላ በማንቸስተር ዩናይትድ እንደሚቆይ ይጠበቃል።
ማይኖ ከዚ በፊት በ አሞሪም የጨዋታ እድል ባለማግኘቱ በውሰት ለመውጣት እያሰበ ነበር።
19/01/2026
ሳዲዮ ማኔ በሜዳ ላይም ከሜዳ ውጪም ጀግንነቱን ያሳየ ልባም እውነተኛ አንበሳ፦
እኔ አለፈልኝ ብሎ የሀገሩን ሰዎች አልረሳም 693 ሺ ዶላር በማውጣት ጥራቱ የጠበቀ ሆስፒታል አስገነባ ለሀገሩ....
ተንደላቀቅኩ ብሎ በትምህርት እጦት የሚሰቃዩ የሀገሩን ልጆች አልረሳም 350 ሺ ዶላር በማውጣት ዘመናዊ ትምህርትቤት አስገነባላቸው....
ጠግቤ አደርኩ ብሎ የሚላስ የሚቀመስ አጥተው የሚራቡትን አብሮ አደጎቹን አልረሳም ባደገባት መንደር ለሚገኙ ሁሉም ቤተሰቦች በወር 70 ዩሮ ወይም 45 ሺ የሴኔጋል ፍራንክ በመለገስ ጠግበው እንዲያድሩ ይረዳል....
በሰለጠነ ሀገር ኖርኩ ብሎ ኋላ የቀረችውን መንደሩን አልረሳም ከአለም እኩል እንዲራመዱ በራሱ ወጪ የ4G ኢንተርኔት አስጀመረላቸው....
ሰርቼ ገንዘብ አገኘሁ ብሎ ስራ አጥ የሀገሩን ልጆች አልረሳም 250 ሺ ዶላር በማውጣት የነዳጅ ማደያ እና ዘመናዊ የዳቦ መጋገሪያ ፋብሪካ በመገንባት በርካቶችን ከስራ አጥነት አላቀቀ...
የእግርኳስ ህይወቱ ስለሰመረለት ህልማቸውን ለማሳካት ዳገት የሆነባቸውን የሀገሩን ልጆች አልረሳም በየወሩ የላፕቶፕ የእግርኳስ ትጥቆች እና የትምህር መሳሪያዎችን ይለግሳል....
ሳዲዮ ማኔ ከእግርኳስ ተጫዋችነትም በላይ የብሩህ ተስፋ እና የቅን ልብ መለኪያ ነው...የአፍሪካ ኩራት የሚለው ቃልም ከሱ በላይ የሚገባው የለም!❤️👏
19/01/2026
ሞሮኮ ከ2000 ጀምሮ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ሪከርድ ፡
2000 - ከምድብ ወደቀች
2002 - ከምድብ ወደቀች
2004 - ሁለተኛ ደረጃ 🥈
2006 - ከምድብ ወደቀች
2008 - ከምድብ ወደቀች
2010 - አላለፉም ነበር ❌
2012 - ከምድብ ወደቀች ❌
2013 - ከምድብ ወደቀች ❌
2015 - ተሰረዘች ❌️
2017 - ሩብ ፍጻሜ ❌
2019 - 16 ጥሎ ማለፍ ❌
2021 - ሩብ ፍጻሜ ❌
2023 - 16 ጥሎ ማለፍ ❌
2025 - ሁለተኛ ደረጃ 🥈
ሞሮኮ እንድታሸነፍ የግድ ውድድሩ በሀገራችን ኢትዮጵያ መደረግ ያለበት ይመስላል ....ምክንያቱም መጨረሻ የበላቸው በእናት ሀገር ኢትዮጵያ ምድር ሰለሆነ 🥹
19/01/2026
🎙የሴኔጋል አሰልጣኝ ፓፓ ቲያው፦
"ተጫዋቾቼን ከሜዳ እንዲወጡ ማዘዜ ስህተት ነበር አፍሬበታለሁ ... እግርኳስን ይቅርታ እጠይቃለው"
ማኔ አተረፈው
18/01/2026
በቀጣይ ሳምንት
ውለታ ዋዪው ማን ዩናይትድ Vs ውለታ ተቀባዩ አርሰናል
ቀጣይ ሳምንት ወንድማማችነት አይኖርም ! በኤምሬትስ ከባድ ፍልሚያ 🫡
18/01/2026
የብራይተን ነዋሪዎች በአትሌት ሀይሌ ስም ቡና ማቅረብ ጀምሩ
⚡️በብራይተን ነዋሪነታቸውን ያደረጉ እንግሊዛዊያን በኢትዮጵያዊው ጀግናው አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ስም "ሀይሌ ኮፊ" የተሰኘ ቡና ለሯጮች መሸጥ መጀመራቸው ተገልጿል።
⚡️"ሀይሌ ኮፊ" የሚል ስያሜን ያገኘው ይህ ቡና በቀድሞ የእንግሊዝ የማራቶን ሯጭ ሪቻርድ ኔርኩር ሀሳብ አመንጪነት ለገበያ መቅረቡ ታውቋል።
⚡️ሪቻርድ ኔርኩር ዘጠኝ አመታትን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በቆየበት ወቅት ከኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሀይሌ ጋር በነበረው ቅርበት ይህ የቢዝነስ ሀሳብ ሊመጣ እንደቻለ ተገልጿል።
"ቡና በኢትዮጵያውያን ባህል ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው" ያለው ኔርኩር ሀይሌ በአለም አቀፍ አትሌቲክስ ያለውን ስም በመጠቀም ቡናን ለሚያዘወትሩ ለአትሌቶች "ሀይሌ ኮፊን" እንደሚያቀርብ ገልጿል። ለሽያጭ የሚቀረበው "ሀይሌ ኮፊ" ምርት "Premium Ethiopian Coffee" የሚል መገለጫ እንደሚኖረው ታውቋል።
"በሀይሌ ኮፊ" ሶስት የተለያዩ የቡና አይነትን ለሯጮች እንደሚቀርብ ሲገለፅ የሻምፒዮኖቹ ምርጫ ፣ Emperor's Delight እና Haile Blend እንደሚሰኙ ተገልጿል። ሀይሌ ኮፊ ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ ለተጠቃሚዎች ለሽያጭ መቅረቡ ተዘግቧል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
1000