Fuuldurri keenya ifa
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fuuldurri keenya ifa, Health/Beauty, Addis Ababa.
01/08/2026
"ወያኔ 'በምዕራብ ትግራይ ብልፅግና አጥቅቶኛል' ብሎ መግለጫ አውጥቷል ሲባል ሰምቼ በጣም ነው የገረመኝ።
እስኪ አስቡት፤ ትናንትና 'የምዕራብ ትግራይ ሉዓላዊ ግዛታችን ተይዞብናል፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት አልተከበረም' ሲል የነበረው ራሱ ህወሃት አልነበረም እንዴ? ታዲያ አሁን ደግሞ በየትኛው ሒሳብ ነው 'በምዕራብ ትግራይ ውጊያ ተከፈተብኝ' ሊል የቻለው? ምዕራብ ትግራይ የሚባለው እኮ በአሁኑ ሰዓት በፌደራል መንግስት እጅ ያለ ቦታ ነው። ወይስ ሱዳን ተሻግሮ ሌላ ምዕራብ ትግራይ አለ እንዴ?
እውነቱን ለመናገር ይህን እርስ በርሱ የሚጋጭ መግለጫ ስሰማ ህወሃቶች በእርግጥም አብደዋል ወደሚል ድምዳሜ ነው የደረስኩት። ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ ሚዛናቸውና ስሌታቸው ፈጽሞ ጠፍቶባቸዋል። ቢያንስ ቢያንስ እንኳን 'ይህ እኮ ሎጂክ የለውም፣ ህዝብ ይታዘበናል' ብሎ የሚነግራቸው አንድ ጤናማ አማካሪ እንዴት ያጣሉ?"
27/07/2026
በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ለውጥ የመጣው በጠመንጃ ሳይሆን በበሰለ የሐሳብ ልውውጥ ነው፡፡
የሰለጠነ እና ሰላማዊ የሐሳብ ትግል ዜጎች ያላቸውን ፖለቲካዊ ልዩነቶች በውይይት፣በድርድር እና በምክክር የሚፈቱበት ስርዓት ነው።
ሰላማዊ የሐሳብ ትግል
🤝🏾 የሰውን ልጅ ክብር የሚጠብቅ
🤝🏾 ልዩነቶችን በሰለጠነ ውይይት የሚፈታ
🤝🏾 ሀገራዊ ሀብታችን ለጥፋት ሳይሆን ለልማት እንዲውል የሚያስችል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡
ሰላማዊ የሐሳብ ትግል
🔸 ለሕግ የበላይነት መስፈን
🔸 ለሀገር ሉዓላዊነት መከበር
🔸 ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት
🔸 ለሕዝቦች ደኅንነት እና መብቶች መጠበቅ
🔸 ሰላም እንዲሰፍን እና ሕጋዊ ተጠያቂነት ያለበት ሥርዓት እንዲኖር ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው።
ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊
21/07/2026
ኢትዮጵያ ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ ግጭት አፈታት እና የእርቅ ሥርዓቶች አሏት!
እነዚህ ሀገር በቀል ጥበቦች ግጭትን ከመፍታት ባለፈ፣ የተቋረጠ መተማመንን እና ማህበራዊ ትስስርን ዳግም ያጠናክራሉ።
🤝 የእርቅ ባህላችን መቻቻልን ያስተምራል
🤝 የሀገር በቀል ጥበቦቻችን ለዘላቂ ሰላም ጠንካራ መሠረት ናቸው።
🤝 ይህንን ውድ ባህል ማደስ እና ለወጣቱ ትውልድ ማስተላለፍ የሁላችንም ኃላፊነት ነው።
የመወያያ ጥያቄዎች 💬
📌 በአካባቢዎ ውጤታማ ሆኖ ያዩት ባህላዊ የእርቅ ወይም የሽምግልና ሥርዓት የትኛው ነው?
📌 የእርቅ ባህላችንን ለዘመኑ ትውልድ በሚገባ ለማስተዋወቅ ምን መደረግ አለበት ብለው ያስባሉ?
ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊
#አስተሳሳሪእሴቶቻችን #ኢትዮጵያ
14/07/2026
14/07/2026
ምላሽዎን በኮሜንት ያሳውቁን! 👇
ሰላም ለኢትዮጵያችን!
Let us know your answer in the comments! 👇
Peace for our Ethiopia!
#ሰላምግንባታ #ሰላማዊነት #ሰላም #ኢትዮጵያ
Click here to claim your Sponsored Listing.