MELA Wellness Center
Empowering Health, Transforming Lives
Email: [email protected]
Phone: 09 09 55 88 77
Visit our website:www.melawellness.org
05/06/2026
The evolution of integrative health requires active validation. Today, we open the doors to our inaugural cohort. This week, we shared how the MELA Integrative Health philosophy is expanding its scope. We believe that medical AI cannot operate safely in a vacuum—it requires the exact same rigorous, whole-system perspective that we apply to human wellness. To bridge the gap between global AI engineering and localized clinical realities, we are building a specialized network of medical professionals trained to mitigate algorithmic hallucination and "resource blindness." Applications are now officially open for the Inaugural MELA Clinical AI Validation Alpha Team. We are extending a professional invitation to clinicians who are ready to evolve from passive AI observers into active AI validators. We are looking for applicants who are: Systems-Level Thinkers: Clinicians who understand complex, holistic patient realities and integrative health. Patient Safety Advocates: Professionals dedicated to ensuring AI algorithms are evidence-based and safe for diverse global environments (including LMICs). Forward-Looking: Medical experts passionate about Reinforcement Learning from Human Feedback (RLHF) and the future of digital health. How to Apply: Please scan the QR code in the image below to access our secure application portal, or use the direct link provided in the comments. We look forward to reviewing your applications and taking this critical step forward together. Hashtags:
Apply here: https://forms.gle/u9VZ7mgcD7SDfDne6
For More Information☎️__09-09-55-88-77
ሁሌ ምዝገባ ሁሌም ትምህርት አለ🙌
11/11/2025
ከፍተኛ የደም ግፊትን ለማስተካከል መከተል የሚያስፈልገው አመጋገብ
1) የጨው አጠቃቀምን በጣም መቀነስ እና በምትኩ የምግብ ጣዕም የሚሰጡ ቅመሞችን መጠቀም
ለምሳሌ:- ነጭ ሽንኩርት፣ እርድ፣ቀረፋ፣ሎሚ...
2)ቀይ ስጋ፣ጮማ፣የወተት ተዋፅዖ...የእንስሳት ተዋፅዖ ፕሮቲን እና ቅባት በጣም መቀነስ
አሳ እና እንቁላል በመጠኑ መጠቀም
3) የተቀነባበሩ የፉርኖ ውጤቶች እና የተለያዩ ማጣፈጫና ቀለም የተጨመረባቸው ምግቦች፣ስኳር፣ በዘይት የተንቸከቸኩ ፈጣን ምግቦች... አለመመገብ
በምትኩ
አትክልት፣ ፍራፍሬ ፣ ጥራጥሬ፣ ከነአሰሩ የተዘጋጁ አህሎች፣ የቅባት እህሎች...ማዘውተር
4) በፖታሽየም፣ ማግኒዚየም እና ካልሽየም የበለጸጉ ምግቦችን ይበልጥ ማዘውተር
ለምሳሌ:- አሳ፣ሙዝ፣እንቁላል(በመጠኑ)
አቮካዶ፣ አረንጓዴ አትክልቶች፣ ስራስሮች፣ ጥራጥሬዎች፣የቅባት እህሎች ...
5) የአልኮልና የካፊን መጠጦችን አለመጠቀም
6)ከአመጋገብ በተጨማሪ የደም ግፊት ለመቀነስ የሚረዱ ኸርባሎችን በመጠኑ መጠቀም
7)ከአመጋገብ በተጨማሪ በቀን ቢያንስ ለ30ደቂቃ የአካል እንቅሰቃሴ ማድረግ
መራመድ፣ሳይክል መንዳት፣ ...
🤔የአካል እንቅስቃሴ ለእነዚህ በሽታዎች ምን ያደርጋል?
ከዋና ዋና የበሽታ መከላከያ መንገዶች መካከል የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ አንደኛው ነው። የበሽታዎችን አስከፊ ውጤት ለመቆጣጠር እና ለመቀነስም ይረዳል።
🥏1. የልብ እና የደም ሥር በሽታዎች
- የልብ እና የአተነፋፈስ ስርዓትን በማስተካከል አጠቃላይ የልብ እና አተነፋፈስ ስርዓቱ ያስተካክላል ።
- ደም ግፊት እና ኮሌስትሮልን ይቆጣጠራል።
- የልብን ጉዳት ይከላከላል።
- የደም ስርጭትን ያሻሽላል።
🥏2. የሁለተኛ ዓይነት የስኳር በሽታ (Type 2 Diabetes)
- የሰውነት ኢንሱሊን አጠቃቀምን ያሻሽላል ።
- የደም ስኳርን በመቆጣጠር ይረዳል ።
- ስኳር በሽታን ይከላከላል።
🥏3. ውፍረት (Obesity)
- ካሎሪ ያቃጥላል።
- የሰውነት የስብ መጠንን ለመቀነስ እና ጤናማ ክብደት ለመጠበቅ ይረዳል።
🥏4. የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች (e.g., Asthma, COPD)
- የመተንፈሻ ችሎታን ያሻሽላል።
- የመተንፈሻ ጡንቻዎችን ያበረታል።
- ጥሩ የአተነፋፈስ ስርዓት እንዲኖረን ያደርጋል።
🥏5. የአእምሮ ጤና (Mental Health)
እንቅስቃሴ በስራ እና ሀሳብ የደከመ አዕምሮን የማደስ አቅም አለው ። የጭንቀት ሆርሞንን (Cortisol) በመቀነስ እንዲሁም ጥሩ እንዲሰማን የሚያደርግ ሆርሞን (Endorphin) በመጨመር የአዕምሮን ጤና ይጠብቃል ።
13/10/2025
💥Diabetes Mellitus💥
11/10/2025
💥💥💥የምስራች መላ የጤናማ ኑሮ ማማከርና ማሰልጠኛ ማዕከል የ
*Pulmonary Function Test እና
*ECG(Electro Cardiography) ምርመራ እጅግ በታላቅ ቅናሽ መስጠት መጀመሩን ስንነግርዎ በደስታ ነው።💥💥💥
የስኳር ሱስ
ልክ እንደ አልኮል፣ መጠጥ፣ ሲጋራ ፣ ካፊን(ቡና)... ሱሶች ስኳርና የተለያዩ አርቴፊሻል ማጣፈጫ የተጨመረባቸው ምግቦች እና ፈጣን የተጠበሱ ምግቦች ሱስ እንደሚሆኑ እና በዚህ ምክንያት ከፍተኛ የረሀብ ስሜት፣ የራስ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣የድካምና የህመም ስሜት፣ ትኩረት ለማድረግ መቸገር፣ ... የመሳሰሉ የህመም ስሜቶች እንደሚያስከትሉ ጥናቶች ያመላክታሉ ።
ከዚያም እነዚህን ምግቦች በተደጋጋሚ የመብላት ፍላጎትን ይጨምራል። ሲበሉም ለጊዜው የረሀብ እና የህመም ስሜቱ ይቀንሳል።
🍔🧇🍟🍕🧈🍡🧁🍰🍩🍪🍿🍫
ነገር ግን እነዚህ ምግቦች ፋይበር እና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ስለሌላቸው ከተመገቡ 2-3 ሰዓት ባልሞላ እንደገና የረሀብ እና የህመም ስሜቱ ይጀምራል። ስለዚህ ሰውነት ከሚያስፈልገው የካሎሪ መጠን በላይ ብዙ መመገብን ያስከትላል ።
ይህን አላስፈላጊ ተጨማሪ የምግብ መጠን ደግሞ ሰውነት ተጠቅሞ ስለማይጨርሰውና የነዚህን አርቴፊሻል ማጣፈጫዎች መርዝ ሰውነታችን በቀላሉ ማስወገድ ስለማይችል በስብ መልክ ያስቀምጠዋል።
ይህም ከመጠን ላለፈ ውፍረት፣ለስኳር ህመም፣ በተለያዩ ባክቴሪያና ጀርሞች በቀላሉ መጠቃት፣ ለልብ ህመምና የደም ግፊት መጨመር፣ የጉበት ስብ መከማቸት፣ ለጥርስ ህመምና መቦርቦር፣ ለሆርሞን መዛባት፣ ለድካምና አቅም ማነስ፣ ብስጩነት፣ ትኩረት ለማድረግ መቸገር፣ የካንሰር ተጋላጭነትን መጨመር....ወዘተ ብዙ የጤና መታወክን ያስከትላል።
🥗🍲🥙🍆🥕🫑🫛🥦🥬🍍🥭🍑🍒🫐🍇🍓🥝🥒🌶🍅🧄🧅
💌ስለዚህ ተፈጥሮአዊ የሆኑና ፋይበርና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ያላቸውን እህሎች፣ ጥራጥሬዎች፣የቅባት አህሎች፣ አረንጓዴ አትክልቶችና ተፈጥሮአዊ ጣፈጭ ያላቸውን ፍራፍሬዎችን በመመገብ ጤናችንን ከሚያውኩና ከማይጠቅሙ ምግቦች እንጠበቅ፤ መልዕክታችን ነው⚠️
ከእኛ ጋር አመጋገብዎን፣ሰውነትዎን እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤዎን ያስተካክሉ ፤ እናግዝዎታለን።
☎️፦ 09 09 55 88 77
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
✅ "ሙቅ ውሃ በተፈጥሮ የተዘጋጀ የቤት ውስጥ ህክምና መስጫ ነው ይሉታል" ጃፓናውያን ማለዳ እንደተነሱ ለብ ያለ ውሃን የመጠጣት ልምድ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን፥ ይህም እጅግ በርካታ ህመሞችን ለማዳን እና ለመከላከል እንደሚያስችልም ነው በተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች ማረጋገጥ የተቻለው።
ለብ ያለ ውሃን መጠጣት ለረዥም ጊዜ ታዋቂ የሆኑ በሽታዎችንና ዘመን አመጣሽ በሽታዎችን ሳይቀር ለማዳንም ሆነ ለመከላከል እንደሚያስችል ጥናቶች አመላክተዋል ።
✏️ለአብነትም
🔘ለጨጓራ ህመም፣
🔘ለብሮንካይትስ፣
🔘ለኩላሊት፣
🔘ለስኳር ህመም፣
🔘ለአስም፣
🔘ለሳምባ ነቀርሳ፣
🔘ለወር አበባ መዛባት
🔘ለምግብ አለመስማማት፣
🔘ለደም ግፊት፣
🔘ለቁርጠት፣
🔘ለካንሰር፣
🔘ለራስ ምታት፣
🔘ፈጣን የልብ ምትን ለማስተካከል፣
🔘ለድርቀት ፣
🔘ማጅራት ገትር በሽታን ለመከላከል፣
🔘ከልክ ላለፈ ውፍረት፣
🔘ለጆሮ፣ አፍንጫ እና ጉሮሮ ህመሞች እና ለሌሎችም ፍቱን ነው።
t.me/melawellnesscenter
በ 0909558877 በመደወል ያማክሩን።
✅ የchia seed የጤና ጥቅሞች
የቺያ ዘሮች ጥቃቅን ናቸው ግን ደግሞ በንጥረ ነገር የተሞሉ ናቸው 🌱.
የ Chia seed ዋና የጤና ጥቅሞች እነሆ:-
1. በ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የተሞሉ ናቸው
ፋይበር, ፕሮቲን, ኦሜጋ -3, ካልሲየም, ማግኒዥየም እና antioxidants በዉስጣቸዉ ይይዛሉ::
2. የምግብ መፈጨት ሂደትን(digestive system) ይደግፋል
ከፍተኛ ፋይበር (በ 2 የሾርባ ማንኪያ ዉስጥ 10 ግራም አካባቢ) በዉስጡ ስላለው የምግብ መፈጨት ሂደትን በማስተካከል ከሆድ ድርቀት ይከላከላል::
3. የስኳር መጠንን ለመቆጣጠር ይረዳል
የሚሟሟው ፋይበር የግሉኮስን absorbtion በማዘግየት በደም ዉስጥ ያለዉን የስኳር መጠን ለማስተካከል ያግዛል::
4. የልብ ጤናን ይደግፋል
ኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ እና ፋይበር ኮሌስትሮልን እና ትራይግላይሴራይድን ለመቀነስ ይረዳሉ::
5. ክብደትን ለማስተካከል
Chia seed በዉሃ ሲዘፈዘፍ ፈሳሹን በመምጠጥ ስለሚበዛ በቶሎ የጥጋብ ስሜት ስለሚፈጥር ብዙ መብላትን በመከላከል ክብደት መጨመርን ለመከላከል ያግዛል::
6. የአጥንት ጤና
በካልሲየም, ፎስፈረስ እና ማግኒዥየም የበለፀጉ ስለሆኑ ለአጥንትና ጥርስ ጥንካሬ አስፈላጊ ነው::
7. ኢነርጂ እና ጽናት
በታሪካዊዎቹ AZTEC እና Mayan ስልጣኔዎች ተዋጊዎቻቸዉ ጉልበት እንዲሰጣቸዉ በማሰብ chia seedን
ይመገቡ ነበር::
8. ቆዳን ከእርጅና ለመከላከል
Chia seed በዉስጡ antioxidants ስላሉት ጤናማ ቆዳን ጠብቆ ለማቆየት ያግዛል::
ከጤና ሁኔታችሁ እና ከምትወስዱት
መድኃኒት አንፃር በምን ያህል መጠን መጠቀም እንደምትችሉ ለማወቅ በዚህ ሊንክ ወይም በ 0909558877 በመደወል ያማክሩን።
16/09/2025
MELA Wellness Center
በጣም ከ ታላቅ ቅናሽ ጋር _CPD_ይመዝገቡ
🖌 Topic: - Integrative prevention and management of Non-communicable Diseases (NCDs)
አስደሳች ዜና ለሁሉም ጤና ባለሙያዎች
**የሙያ ፍቃዳችሁን ላላሳደሳችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ ✅
*** ልዩ የሚያደርጉን ***
👌 1ኛ ልዩ የሚያደርገን ተመጣጣኝ ዋጋ (Benefit packages)
15 CEU =400 BIRR
30 CEU=900 BIRR
45 CEU=1400 BIRR
60 CEU=1900 BIRR
👌 2ኛ ልዩ የሚያደርገን በጤና ሚኒስቴር እውቅና ያለው የ CPD ስልጠናዎች የሚቀርቡበት ማዕከል መሆኑ
For All department (ለሁሉም ዲፓርትመንት)
1. GP
2. HO
3. Nutrition/Dietician
4. Anesthesia
5. Nurse
6. Midwifery
7.Pharmacy
8. Laboratory
9. others health professional
👌 3ኛ ልዩ የሚደርገን ሁሌም ምዝገባ ሁሌም ስልጠና አለ፡፡
👌 4ኛ ካሻዎት online በምንሰጠው ስልጠና ባሉበት ሆነው የሚፈልጉትን CEU ነጥቦች እንዲያሟሉ እናግዛለን፡፡
👉Training starts: on September 02, 2025 (ነሃሴ 26፣2017 ዓ.ም)
👉 There will be special discount for those who come in group.
ለበለጠ መረጃ
📱 +251909558877
እንዲሁም
በቴሌግራም ያናግሩን
አድራሻ ፡ ቦሌ ቡልቡላ 40/60 ኮንዶሚኒየም ብሎክ 33 የቤት ቁጥር 004
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
1000