Qali Miftac

Qali Miftac

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Qali Miftac, Health/Beauty, Addis Ababa.

29/12/2025

ልዩ ዜና

👉የአርሚ 11 እና አርሚ 13 አዛዦች የጄነራል ታደሰ ወረደን ስብሰባ ረግጠው ወጡ!
👉በጊዜያዊ አስተዳደሩና በፅንፈኛው ቡድን መካከል ያለው ልዩነት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሷል!

የህወሃት ጉዳይ በጣም የሚያስገርም እንዲሆን የሚያሳዝን ሆኗል። ጌታቸው ረዳን አንፈልግም ታደሰ ወረደ ካልሆነ የአለም መጨረሻ ይሆናል ሲሉ የነበሩ ፅንፈኛው የህወሃት የፖለቲካ እና የታጣቂ አመራሮች በጄነራሉ ላይ ተነስተውበታል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጀ/ል ታደሰ ወረደ በታህሳስ 19/2018 ዓ.ም ከህወሓት ታጣቂ ቡድን የምዕራብ ግንባር የአርሚ አዛዦች እና ሎጂስቲክስ አመራሮች ጋር በሽሬ ከተማ ስብሰባ አካሂዶ ነበር። ይህ ስብሰባ በዋናነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጊዜያዊ አስተዳደሩና በጽንፈኛው ቡድን መካከል እየታዩ የሚገኙ ልዩነቶችን ለመድፈን ያሰበ ቢሆንም ልዩነቶች የበለጠ የሰፉበትና ከፍተኛ መካረር የተፈጠረበት መሆኑን ከታማኝ ምንጭ ማረጋገጥ ተችሏል።

በተለይም የአርሚ 13 አዛዥ ፀጋዬ ማርከስ እና የአርሚ 11 አአዛዥ ፍስሃ ኪዳኑ (ወርቅ አይኑ) ጀ/ል ታደሰ በስብሰባው ያቀረበውን ሃሳብ ባለመቀበል ስብሰባውን አቋረጠው የወጡ መሆናቸውን ማወቅ ተችሏል። እስካሁን ባለው መረጃ ምንም እንኳን ስብሰባውን ረግጠው የወጡት ሁለት የአርሚ አዛዦች ቢሆን ሌሎች ተጨማሪ ከፍተኛ የቡድኑ አመራሮች የፕሬዘዳንቱን ሃሳብ ያለመቀበል አዝማሚያ እየታየባቸውና በቀጣይ ቀናትም ልዩነቱ ተባብሶ እንደሚቀጥል ይስተዋላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ እነዚህ የአርሚ አዛዦች በፕሬዘዳንቱ ላይ መፈንቅለ መንግስት ሊፈፅሙ ይችላሉ በሚል በመቀሌ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa