Ethiopian for African
INTERNATIONAL MINDS
15/09/2026
አዲስ አበባ ወደ ስማርት ሲቲ (ዘመናዊ ከተማ) ለመቀየር በምታደርገው ተከታታይ ጥረትና በምታስመዘግባቸው ስኬቶች በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችንና እውቅናዎችንም አግኝታለች።
ከእነዚህ እውቅናዎች መካከልም :-
👉 በሪዮዲጀነሪዮ የተቀበለችው የምገባ ኘሮግራም ሽልማት፣
👉 በደቡብ ኮሪያ የተበረከተውና ለከተማዋ አመራር እውቅና የሰጠው የሴኡል ስማርት ከተማ ሽልማት (2024)፣
👉 ለቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት መሻሻል በቦነስአይረስ የተሰጠው እውቅና፣
👉 የC40 ከተሞች የብሉምበርግ ሽልማት፣
👉 በናይሮቢ ኬንያ በተካሄደው የአፍሪካ ስማርት ከተሞች ኢንቨስትመንት ሰሚት የተሰጠው የአፍሪካ ምርጥ ስማርት ከተማ ሽልማት (2024)፣
👉 አዲስ አበባ በመንገድ ደህንነትና ፍጥነት ማስተዳደር ላይ ባስመዘገበችው ውጤት በዓለም አቀፍ የከተሞች የዘርፉ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችባቸው ተጠቃሽ ናቸው፡፡
እነዚህ ዓለም አቀፍ እውቅናዎች የከተማዋን ሁለንተናዊ መልካም ገጽታ በዓለም መድረክ ላይ በግልጽ ያሳዩ ታላላቅ ስኬቶች ናቸው።
በዚህ መሰረትም ዓለምዓቀፍ ተቋማቶች ስብሰባዎቻቸውን አዲስ አበባ ላይ ለማድረግ ቀዳሚ ምርጫቸውን አድርገዋል፡፡ በ2018 በጀት ዓመት ብቻ 221 ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፈረንሶች በአዲስ አበባ መካሄዳቸውን አዲስ አበባ ያለችበትን ደረጃ በትክክል የሚገልፅ ነው፡፡
15/09/2026
ብልፅግና ፓርቲ ተግዳሮቶችን በድል በመሻገር ላስመዘገባቸው ውጤቶች የወጣቶች ክንፍ ሚና ከፍተኛ ነው! -አቶ አብርሃም ታደሰ
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ጋር በ2019 ዕቅድ እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ተግባቦት መድረክ አካሄደ።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ጠንካራ የወጣት ተሳትፎ ለዳበረ ዴሞክራሲ ፣ ለአገልግሎት መሳለጥ እና ለልማት መፋጠን ወሳኝ በመሆኑ ብልፅግና ፓርቲ ለወጣቶች ክንፍ አደረጃጀት መጠናከር ልዩ ትኩረት ሰጥቷል።
ብልፅግና ፓርቲ ተግዳሮቶችን በድል በመሻገር ላስመዘገባቸው ውጤቶች ወጣቶች ክንፍ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የጠቀሱት አቶ አብርሃም በቀጣይም ድርብርብ ተልዕኮዎችን አልቆ መፈፀም እንደሚገባው አመላክተዋል።
የፓርቲያችንን እሳቤዎች በማስረፅ፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በማጠናከር፣ ተተኪ አመራሮች በመፍጠር፣ በወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚነት እንዲሁም በሌሎችም የሰላምና የልማት ስራዎች ክንፉ ግንባር ቀደም ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ወጣት መለሰ አባተ በ 2018 በጀት ዓመት
የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በስራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት፣ ማህበራዊ ተሳትፏቸውን እንዲያጎለብቱ በተለይም በበጎ ፈቃድ ተግባራት እንዲሁም የወጣቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማሳደግና ክንፉን የአመራር ቋት ከማድረግ አኳያ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸው ጠቅሰዋል።
ከመደበኛ ስራዎች ባሻገር የወጣቶች ክንፍ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ተልዕኮውን በአግባቡ መወጣቱን ያወሱት ወጣት መለሰ በክፍለ ከተሞች መካከል ተቀራራቢ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።
ተቋም ግንባታ በአዲሱ በጀት ዓመትም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን የጠቆሙት ወጣት መለሰ ከችግሮች በመቆራረጥ፣ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል የላቀ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችል የመልሶ ማደራጀት ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
የወጣቶችንን ሁለንተናዊ አቅም በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እንዲሁም ፖለቲካዊ ተሳትፎን ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ ያስገነዘቡት ወጣት መለሰ ዕቅዱን የተግባር መመሪያ በማድረግ መደበኛና የንቅናቄ ስራዎችን አቀናጅቶ መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ም/ ኃላፊ ወጣት በቀለ ታጀብ በበኩላቸው ባለፈው ዓመት የወጣቶች ክንፍን ተቋማዊ ቁመና መፈተሽ ያስቻሉ ሀገራዊና ከተማዊ ሁነቶች መከናወናቸውን ጠቅሰው የብልፅግና ፓርቲን እሳቤዎች በተግባር ለመተግበር ፣ ተልዕኮዎችን ለማሳካት ተቋማዊ አደረጃጀትን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አዲሱ ዓመት ብልፅግና ፓርቲ ለህዝባችን የገባውን ቃል አልቆ መፈፀም የሚጀምርበት ዓመት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ወጣቶች ክንፍ ተቋማዊ አቅሙን በማጠናከር የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንዲሁም የወጣቶችን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎ ለማጠናክር በትኩረት እንደሚሰራ ተጠቅሷል።
በተለያዩ አማራጮች የወል ትርክትን ለማስረፅ፣ ተኪ አመራሮችን ለማበራከት እና በሌሎችም የሰላምና የልማት ስራዎች የተቀናጀ ርብርብ፣ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወጣት አንሙት አበጀ ባቀረቡት የክንፉ ዕቅድ ተመላክቷል።
የወጣቶች ክንፍ የከተማ፣ የክ/ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ዕቅዱን ይበልጥ የሚያዳብሩ ሀሳቦች በመስ
Ethiopian for African
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹💫💫💫👇❤❤
15/09/2026
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
14/09/2026
Ethiopian for African
ብቻ
13/09/2026
🇪🇹🤝🇷🇺 **ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ እያሳየች ያለችው ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት እና የብሪክስ (BRICS) አባልነት ስኬት!**
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግሥት አገራችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ላቀፈቻቸው ስትራቴጂካዊ ስኬቶች ምስጋና ይገባዋል። በኒው ዴልሂ በተካሄደው የብሪክስ ጉባዔ ጎን ለጎን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላዲሚርፑቲን ከጠቅላይ ሚኒስትራችን ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን አገራዊና ቀጣናዊ ሚና አድናንቀዋል።
📌 **የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች፡**
* **ሁለትዮሽ ንግድና ኢኮኖሚ፡** በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ በሦስት እጥፍ ማደጉ መንግሥት የተከተለው ነፃና ፍትሐዊ ዲፕሎማሲ ውጤት ማምጣቱን ያሳያል።
* **ፍትሐዊ የዓለም ሥርዓት፡** ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ከመሆኗ ጀምሮ የዓለም አቀፉን የኃይል ሚዛን ለማስተካከልና የብዙኃኑን ድምፅ ለማስደመጥ በንቃት እየሠራች ትገኛለች።
* **ታሪካዊና ዘላቂ ወዳጅነት፡** የሁለቱ አገራት ወዳጅነት በእኩልነትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ተመሥርቶ ከትምህርት እስከ ኢኮኖሚ በጠንካራ መሠረት ላይ ይገኛል።
ኢትዮጵያ በብልህ መሪዎቿ አማካኝነት ታላቅነቷን እየመለሰች ይገኛል!
መልካም አዲስ ዓመት 2019 ዓ.ም! 🌼🇪🇹
#ኢትዮጵያ #ዲፕሎማሲ
13/09/2026
በብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር የተደረገ ውይይት።
🇪🇹 🇨🇳
Conversations with China’s President Xi Jinping on the sidelines of the BRICS Summit.
🇪🇹 🇨🇳
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
12/09/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ
Category
Website
Address
GOOD
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian for African posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.