About Ethiopians

About Ethiopians

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from About Ethiopians, Health/Beauty, Addis Ababa.

22/07/2026

ኦነግ ህወሓትን አስጠነቀቀ፣ የህወሓት ተስፋ መነመነ፣ የቀራቸው አንድ ኢሕአፓ ብቻ ነው

16/07/2026

ኢትዮጵያውያን ለመመካከር በጠረጴዛ ዙርያ ተገኝተዋል

ዛሬ ኢትዮጵያ ታሪካዊ በሆነና አዲስ ምዕራፍ በሚከፍት ብሄራዊ ምክክር ላይ ትገኛለች። ይህ መድረክ የቆዩ ቁስሎችን ለመፈወስ፣ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ ለማስታረቅና የጋራ የወደፊት እጣ ፈንታችንን ለመወሰን የተዘረጋ ታላቅ የሰላም ድልድይ ነው።

የዚህ ምክክር ዋነኛ ጥንካሬና አስገራሚ ገጽታ ደግሞ ፍጹም ሁሉንም ያካተተ መሆኑ ነው። ከእያንዳንዱ የሀገሪቱ አቅጣጫ—ከምስራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ—የተወጣጡና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚወክሉ አጀንዳዎች ለውይይት ቀርበዋል። የቀረቡት አጀንዳዎች የአንድ ወገን ብቻ ሳይሆኑ የብዝሃነታችን፣ የጋራ ስጋቶቻችንና የወደፊት ተስፋዎቻችን እውነተኛ ነጸብራቅ ናቸው።

በዚህ ታሪካዊ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ላይ የተሰበሰቡት ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን ሙሉ ገጽታና ህብረ-ቀለማት የሚገልጹ ናቸው። ድምፃቸው ተደፍኖ የኖሩ ዜጎችን፣ አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን ስሜትና እውነተኛ ህመም አንግበው የቀረቡ የህብረተሰብ ተወካዮች የመድረኩ ዋነኛ ተዋናይ መሆን ችለዋል። ከእነሱም ጎን ለጎን፣ በታማኝነታቸውና በክብራቸው የታወቁ የሀገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦች በመገኘት የሽምግልና እና የትዕግስት ባህላችንን እያደሱ ይገኛሉ።

ውይይቱ በስሜት ብቻ ሳይሆን በዕውቀት፣ በምክንያታዊነትና በሳይንሳዊ እይታዎች ላይ ተመስርቶ የበሰለ መፍትሄ እንዲያመጣ ደግሞ ምሁራንና ባለሙያዎች የላቀ ሚናቸውን እያበረከቱ ነው። በተጨማሪም ሴቶች፣ ወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች ጭምር የነገዋን ሀገር በጋራ ለመገንባት በንቃትና በእኩልነት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ይህ ታላቅ መድረክ በጉልበት ሳይሆን በሃሳብ የበላይነት፣ በጠላትነት ከመተያየት ወጥተን እርስ በርስ በመደማመጥ የጋራ ቤታችንን የምንገነባበት ወርቃማ አጋጣሚ ነው። ዛሬ በሰላም ለመመካከርና ለመወያየት የተቀመጠችው ኢትዮጵያ፣ ነገ በልጆቿ ምክክርና የጋራ መግባባት ላይ ጸንታ የምትቀጥል የበለጸገችና ጠንካራ ሀገር ለመሆን የመጀመሪያውንና ዋነኛውን መሰረት እየጣለች ትገኛለች።

የምትፀና_ሀገር

07/07/2026

ተሰናባቹ የፓርላማ አባል 5ዓመታትን የረባ ያልረባ ጥያቄዎችን በማንሳት የእለት ጭብጨባ ፈላጊውና የጽንፈኞች መጠቀሚያ ሆኖ የቆየው ደሳለኝ ጫኔ እነሆ በጩኸትና በለቅሶ አንዳች ለውጥ ማምጣት ሳይችል ቀርቶ 5ዓመታትን ካባከነ በኋላ በመጨረሻ የመሰናበቻ ግዜው ጸጉሩን አስተክሎ ለውጡ ጸጉር ማስተከል ብቻ መሆኑን አሳይቶናል! መክሸፍ እንደ ደሳለኝ ማለት ይህን ግዜ ነው! ሀገር የሚለውጥ ስራ ለመስራት እንጂ ፀጉር ለማስተከልኮ ፓርላማ መግባትም አያስፈልግም ነበር፡፡ ዮኒ ማኛም አስተክሏልና!😀🥹

03/07/2026

ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች በሙሉ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤውን ከሀምሌ 8 /2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚያካሂድ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በመሆኑም በጉባኤው ለመሳተፍ የተመረጣችሁ በሙሉ በተደረገላችሁ ጥሪ መሰረት ሀምሌ 1/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገብታችሁ ሪፓርት እንድታደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪ ያቀርባል።

የጉባኤው ቆይታ ከ3 ሳምንታት እስከ አንድ ወር ስለሚቆይ ለዚህ ጊዜ የሚሆን ዝግጅት አድርጋችሁ እንድትመጡም ኮሚሽኑ ያሳውቃል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን!

Photos from About Ethiopians's post 27/06/2026

የከተማ አስተዳደሩ የድሆችን ቤት የቀሙ አመራሮችን ከኃላፊነታቸው በማንሳት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ ተበዳዮችን ወደ ቤታቸው መለሰ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ (ወረዳ 5) የተሰጣቸውን የህዝብ አደራ ወደ ጎን በመተው፣ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ነዋሪዎችን ለዘመናት ከኖሩበት የቀበሌ ቤት ያፈናቀሉ 3 የክፍለ ከተማ እና 2 የወረዳ አመራሮችን ተጠያቂ በማድረግ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱና በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

ኃላፊነታቸውን ያለአግባብ የተጠቀሙ አመራሮች፣ የካንሰር እና የልብ ህመምተኛ የሆኑ አቅመ-ደካሞችን ጨምሮ በርካታ ነዋሪዎችን በውድቅት ሌሊት እና በማለዳ በፖሊስ እና በኮንስትራክሽን ወዛደሮች አስከብበው፣ ንብረታቸውን በትነው ጎዳና ላይ እንደጣሏቸው ተበዳዮች ተናግረዋል።

የወረዳው ነዋሪ የሆኑት እናት፣ ወልደዉ በተኙበት ፖሊስ ከቤታቸዉ አውጥቶ እንደስወጣቸዉ ገልጸዋል።

ሌላኛዋ የካንሰር ታማሚ በበኩላቸዉ፣ ፖሊስ ልጃቸዉን ጭምር አስፈራርቶ ከቤት እንዳስወጣቸዉ ነዉ የተናገሩት።

ይህንኑ ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበላይ ኃላፊዎች ጉዳዩን በአስቸኳይ አጣርተው፣ የተፈጸመው በደል በፍጥነት እንዲታረም እና ተበዳዮቹ በአስቸኳይ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ አድርገዋል።

ይህንን የፈፀሙ አመራሮችም ተጠያቂነትን በማስፈንም በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ ሐሰን እንደገለጹት፣ "መንግስት ቤት ሰርቶ ለድሆች ይሰጣል እንጂ ከቤት ደሀ አስወጥቶ ራሱ የሚገባበት አመራር የለውም" በማለት በጥፋተኞቹ ላይ የማያዳግም ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱንና ተጠያቂነቱ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ቤታቸው የተመለሰላቸው እና ፍትህ ያገኙት ነዋሪዎችም ለከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ለከተማው አስተዳደር ምስጋና አቅርበዋል።

በከንቲባ ጽሕፈት ቤት የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አባይነህ አመርጎ፣ አመራሩ የህዝብ አገልጋይ እንደመሆኑ በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል አለበት ያሉ ሲሆን፣ ህብረተሰቡም መሰል የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ለከተማ አስተዳደሩ ተገቢውን እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የምንኖረውም ህዝብ ውስጥ እንደመሆኑ መጠን፣ ስናጠፋም መልካም ስንሰራም ህብረተሰቡ በቅርበት ይከታተለናል ያሉት አቶ አባይነህ፣ ሁሉም አመራር ይሄን ተረድቶ በተሰጠው ኃላፊነት ህዝብን በቅንነት ማገልገል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

Photos from About Ethiopians's post 25/06/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያለፉ ዓመታት የፋይናንስ ጉዞ፣ ከገቢ ማሳደግ እስከ ልማት ተኮር የበጀት ሽግግር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ2010 እስከ 2019 በጀት ዓመት ያሳየው የፋይናንስ መረጃ፣ ከተማዋ በታሪኳ አይታው የማታውቀውን የኢኮኖሚ ዕድገትና መዋቅራዊ ሽግግር እያደረገች መሆኑን በግልጽ ያሳያል። ይህ የ10 ዓመታት ጉዞ ጠንካራ የገቢ አሰባሰብ አቅምን ከመገንባት ባለፈ፣ በጀትን አስተዳደራዊ ወጪዎችን በመቀነስ ለዘላቂ ልማት (ካፒታል) የማዋል ጤናማ የፋይናንስ ፖሊሲን የተገበረበት ነው።

መረጃዎቹ እንደሚያሳዩት፣ በ2010 በጀት ዓመት 40.5 ቢሊዮን ብር የነበረው የከተማዋ አጠቃላይ በጀት፣ በ2019 ወደ 502.27 ቢሊዮን ብር አድጓል። ይህ የ461.77 ቢሊዮን ብር (የ1140 በመቶ) አስደናቂ ዕድገት ሊመዘገብ የቻለው ከተማ አስተዳደሩ የገቢ አሰባሰብ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደጉ ነው።

በ2010 30 ቢሊዮን ብር ብቻ የነበረው የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም፣ በ1574.23 በመቶ (በ472.27 ቢሊዮን ብር) በማደግ በ2019 በጀቱን በሙሉ በራስ አቅም መሸፈን ወደሚያስችልበት ደረጃ ደርሷል። ይህ የገቢ ዕድገት እና የአጠቃላይ በጀት ዕድገት መመጣጠን፣ ከተማዋ የፋይናንስ ሉዓላዊነቷን ማረጋገጧን እና በውስጥ አቅም ፕሮጀክቶችን የማስፈጸም ብቃቷ መጎልበቱን ያመላክታል።

ከቁጥራዊ ዕድገት ባሻገር፣ የከተማዋን የልማት ራዕይ ይበልጥ የሚያጎላው የበጀት ድልድል ስብጥር (Capital vs. Regular Budget) ለውጥ ነው። በ2010 የነበረው የካፒታል በጀት ድርሻ 53.18 በመቶ (21.53 ቢሊዮን ብር) የነበረ ሲሆን፣ ለመደበኛ ወይም ለሥራ ማስኬጃ 46.82 በመቶ (18.96 ቢሊዮን ብር) ይውል ነበር።

ነገር ግን በ2019 ይህ ምጣኔ መሠረታዊ ለውጥ አሳይቶ፣ የካፒታል በጀቱ ድርሻ ወደ 71 በመቶ (355.52 ቢሊዮን ብር) ሲያድግ፣ የመደበኛ በጀቱ ድርሻ ወደ 29 በመቶ (146.74 ቢሊዮን ብር) ዝቅ ብሏል። የአስተዳደራዊ ወጪዎችን (መደበኛ በጀት) በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ የገንዘቡን አብዛኛውን እጅ ለመሠረተ ልማት እና ለትልልቅ ፕሮጀክቶች (ካፒታል በጀት) መዋሉ፣ ከተማዋ ፊቷን ሙሉ በሙሉ ወደ እድገትና ብልፅግና ላይ ለሚታይ ትክክለኛ ልማት ማዞሯን የሚያረጋግጥ የፖሊሲ ስኬት ነው።

በአጠቃላይ፣ እነዚህ መረጃዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሀብት አሰባሰብ አቅሙን እጅግ በላቀ ሁኔታ ከማስፋቱም በላይ፣ የተሰበሰበውን ሀብት በአግባቡ ቆጥቦ የነዋሪዎችን ኑሮ ለሚቀይሩ እና ከተማዋን ለሚያዘምኑ የካፒታል ፕሮጀክቶች ቅድሚያ በመስጠት ከፍተኛ የአመራር ብቃት እያሳየ መሆኑን በተጨባጭ የሚያስረዱ ናቸው።

18/06/2026

“አዲስ አበባ ለመኖር ምርጥ ከሆኑ ከተሞች አንዷ ትሆናለች!”

አዲስ አበባ፥ በሚቀጥሉት 5 እና 10 ዓመታት፣ ከአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ከመላው ዓለም ለመኖር ምርጥ ከሆኑ ከተሞች አንዷ ትሆናለች።

08/06/2026
05/06/2026

የጥፋት ኃይሉ የዲጂታል ክሽፈት

እራሳቸውን 'አርበኛ' ብለው የሚጠሩት የጥፋት ኃይል አባላት (ሀብቴ፣ ሃብታሙ ዮሱፍ፣ ተስፋዬ ልሳኑ፣ አማረ፣ ሰለሞን ወልደገሪማ፣ ሙሉጌታ ደሳለኝ፣ ኪሮስ፣ ያውቃል እና ፋኒት መታደል) በቅርቡ ባካሄዱት ስብሰባ፤ በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት በከፍተኛ ሁኔታ እያጡ መምጣታቸውን አምነዋል።

እነዚህ ህገ-ወጥ ኃይሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች (በተለይም በWhatsApp እና TikTok) ሲያራምዱት የነበረው የብጥብጥ እና የሀሰት ትርክት አጀንዳ፣ ከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ ማነስ እንዳጋጠመውና ክፉኛ መክሸፉን በስፋት መገምገማቸው ታውቋል። ይህ ሁኔታ ህብረተሰቡ ከፀረ-ሰላም ኃይሎች የጥፋት ጥሪ ራሱን ሙሉ በሙሉ እያገለለ እና ለመንግስት የሰላም ጥሪ ቅድሚያ እየሰጠ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa