mn adiss
Ethiopian
27/09/2026
ጦርነት ባህሪው የሆነው የህወሀት የጥፋት ሃይል በራያ ግምባር የጀመረውን ትንኮሳ በመመከት ላይ የሚገኘው የመከላከያ ሃይል ባካሄደው ፀረ-ማጥቃት ዘመቻ በጠላት ላይ ድል በመቀዳጀት ወደፊት በመገስገስ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።
በጥፋት ሃይሉ የደረሰ ኪሳራ;
01 ዲሽቃ
11 ብሬን
13 ክላሽ
01 ስናይፐር
01 መገናኛ ሬዲዮ
21 የእጅ ቦንብ
20 ሺህ በላይ የመትረየስ ጥይት
08 የብሬን ሸንሸል
950 የክላሽ ጥይት
01 የብሬን ካዝና
650 የዲሽቃ ጥይት
06 የዲሽቃ ሸንሸል
03 የዲሽቃ ካዝና
06 ሳጥን የድሽቃ ጥይት
22 የክላሽ ካዝና
05 የክላሽ ትጥቅ እና 03 የመገናኛ ራድዮ ቻርጀር ከጠላት መማረኩ ታውቋል።
27/09/2026
ሰበር ዜና-
የሀገር መከላከያ ሠራዊት አላማጣን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ወደ መኾኒ እየገሰገሰ ነው
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ትናንት የራያ አላማጣ አካባቢዎችን ከተቆጣጠረ በኋላ በዛሬው ዕለት አላማጣ ከተማን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ ወደ መኾኒ ግስጋሴውን ቀጥሏል።
በደረሰን መረጃ መሠረት፤ የአላማጣ ከተማ ከንቲባ ሞገስ ሽፈራው እና አስተዳዳሪው ዝናቡ ገብረመድህን ከተማዋን ለቀው ቀደም ብለው ወደ መኾኒ የሸሹ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ መኾኒንም ለቀው ወደ መቀሌ ማምራታቸው ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ከውጊያው የተረፉ የሕወሓት ታጣቂዎች በጋርጀለ እና በታኦ በኩል በመበታተን ማረፊያቸውን ወደ መኾኒ እና ማይጨው ማድረጋቸው ታውቋል።
27/09/2026
26/09/2026
እንኳን ለደመራና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
የከተማችን ድምቀት ከሆኑ የአደባባይ በዓላት አንዱ ለሆነውና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ለተመዘገበው ለመስቀል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳቸሁ!!
በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በባህላዊ አልባሳቶቻችን ደምቆ፣ የቱሪዝም ስበት ሆኖ የሀገራችንን መልካም ገጽታ በሚያጎላ መልክ ይከበራል።
እንደ ወትሮዉ ሁሉ በአሉን ስናከብር እንደ ዳመራዉ በአብሮነት ተደምረን ፣በትብብር ፣በመተሳሰብ እና በፍቅር እንድናከብር መልካም ምኞቴን አገልጻለሁ።
በድጋሚ እንኳን ለደመራ እና ለመሰቀል በዓል በሳለም አደረሳቸሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን አና ህዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
26/09/2026
እንኳን ለደመራና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
የከተማችን ድምቀት ከሆኑ የአደባባይ በዓላት አንዱ ለሆነውና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ለተመዘገበው ለመስቀል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳቸሁ!!
በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በባህላዊ አልባሳቶቻችን ደምቆ፣ የቱሪዝም ስበት ሆኖ የሀገራችንን መልካም ገጽታ በሚያጎላ መልክ ይከበራል።
እንደ ወትሮዉ ሁሉ በአሉን ስናከብር እንደ ዳመራዉ በአብሮነት ተደምረን ፣በትብብር ፣በመተሳሰብ እና በፍቅር እንድናከብር መልካም ምኞቴን አገልጻለሁ።
በድጋሚ እንኳን ለደመራ እና መሰቀል በዓል በሰላም አደረሳቸሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !
Baga Ayyaana Daamaraa fi Masqalaaf Nagaan Geessan, Geenye!
Miidhagina magaalaa keenyaa kan ta'an ayyaana addabaabayii keessa tokko kan ta'ee fi Dhaabbata Barnoota, Saayinsii fi Aadaa Mootummoota Gamtoomanii UNESCO, hambaa killayyaatti kan galmaa'e ayyaana Masqalaaf baga nagaan geessan!!
Ayyaanichi duudhaa amantichaa eeggatee, uffata aadaa keenyaan miidhagee, hawwata turizmii ta'ee bifa fuula gaarii biyya keenyaa mul'isuun kabajama.
Akkuma durii ayyaana hunda wayita kabajnu akkuma Daamaraa waliin ida'amnee, tumsaan, waliif yaaduu fi jaalalaan akka kabajnu hawwii kiyya gaariin ibsa.
Irra deebiin baga ayyaana Daamaraa fi Masqalaa nagaan geessan!
Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu!
26/09/2026
የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉ.ህ.ዴ.ን) የታጠቁ ሐይሎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች የፈጠሩትን ‹‹ትብብር ለህልውና››የተባለ ጥምረት ውስጥ የለሁበትም አለ።
የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉ.ህ.ዴ.ን) ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥምረት ፈጠሩ የተባሉ ሰባት የታጣቁ ሐይሎችና ፖለቲከኞች ፓርቲው በማያውቀው ጉዳይ ስሙን ማካተታቸውን አስታውቋል፡፡ መስከረም10/2019 ዓ.ም ሰባት የታጣቁ ሐይሎች ፈጥረናል ያሉት ጥምረት ውስጥ ስሙ የተካተተው የጉሙዝ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ጉ.ህ.ዴ.ን) ድርጊቱን አውግዟል፡፡
ፓርቲው ጥምረት ከፈጠሩት ሀይሎች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደለለው በመግለጽ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና ያለውና በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በመሳተፍ 14 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ማሸነፉን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ አመልክተዋል፡፡
26/09/2026
ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ
የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር በዓል ነው። በዓሉ ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ ቀለም አለው። ቤተሰብ ይገናኝበታል። ሠፈሩ ይሰባሰብበታል። ከተማውና አካባቢው ወደ አንድ አደባባይ ይተምበታል። ከእንጨት እስከ ደመራ ያለው መሰባሰብም የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ተምሳሌት ነው።
በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያን ዐቅሞች እያሰባሰብንና እየደመርን ታላቅ ሀገራዊ ዐቅም ለመፍጠር እንትጋ።
በድጋሚ መልካም በዓል ይሁን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16፣ 2019 ዓ.ም
Baga ayyaana Masqalaatiin isin gahe!
Ayyaanni Masqalaa ayyaana karaa amantaafi aadaatiin guutummaa Itoophiyaatti kabajamudha. Ayyaanichi bifa maatummaafi hawaasummaa qaba. Maatiin kan itti walargudha. Mandarris kan itti walgahudha. Magaalaafi naannawaan gara Addabaabayii tokkootti yeroo itti yaa'udha. Walittiqabamuun mukaa hamma damaraatti jirus fakkeenya humna ida'amuu agarsiisudha. Wayita hunda ayyaanicha yoo kabajnu humnoota Itoophiyaa walittiqabneefi idaanee humna guddaa biyyaalessaa uumuuf haadhimmamnu.
Irradeebiidhaan ayyaana gaarii!
Itoophiyaan tattaaffii ijoolleesheetiin sodaatamteefi kabajamtee bara baraan haajiraattu!!
Uumaan Itoophiyaafi uummattootashee haaeebbisu!
Fulbaana 16/2019.
25/09/2026
የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ።
መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ረፋድ ከ5:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-
• ከ 22 ማዞሪያ ወደ መስቀል አደባባይ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች
• ከቦሌ ኤርፖርት ወደ መስቀል አደባባይ ደንበል ወይም ኦሎምፒያ ላይ እና ታች
• ከጎፋ ፣ በታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መሰቀል አደባባይ ለገሃር መብራት
• ከለገሃር ቴሌ ወደ ስታዲየም ንግድ ባንክ ክቡ ህንጻ መስቀለኛ
• ከቸርቸል ጎዳና ፣ በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት ላይ
• ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መስቀለኛ
• ከካዛንቺስ መብራት ወደ መስቀለኛ መቅረዝ ሆስፒታል የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል።
ነገ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
Category
Website
Address
Addis Ababa